Latest

የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ሉላዊ የሞት ቁጥር በ 15 ፐርሰንት ቀንሷል፣ የአውስትራሊያ አረጋውያን ክብካቤ ተቋማት ተጨማሪ ድጎማ ሊያገኙ ነው

ይህ የአውስትራሊያ ኦገስት 25 የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ነው።

COVID19 AGED CARE ADF SUPPORT

Royal Australian Navy sailors speaking with Western Australia aged-care facility residents as part of Operation COVID-19 Assist. (AAP Image/Supplied by Australian Defence Force) Credit: LSIS ERNESTO SANCHEZ/PR IMAGE

አንኳሮች
  • አውስትራሊያ እገዛዋን ለአረጋውያውያን ክብካቤ መኖሪያ ቤቶች እስከ ዲሴምበር 31 አራዘመች
  • በወረርሽኙ ወቅት የሰነት አካላት ልገሳ ቀነሷል
  • የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ከዳግም ኮቪድ አገገሙ
ሐሙስ ዕለት፣ አውስትራሊያ ውስጥ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 29 ኩዊንስላንድ ውስጥ 12 ሕይወታቸው በኮቪድ -19 ያለፉትን ጨምሮ አውስትራሊያ ውስጥ 43 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተመዝግቧል።

የአውስትራሊያን በኮቪድ -19 አዲስ ተጠቂዎች፣ ለሆስፒታል የተዳረጉትና ለሕልፈተ ሕይወት የበቁትን ወቅታዊ ሂደቶች እዚህ ይመልከቱ።
የአውስትራሊያ መንግሥት መሥፈሩን ለሚያሟሉ የአረጋውያን ክብካቤ አገልግሎት ሰጪዎች የኮቪድ - 19ኝን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችል ተጨማሪ ድጎማ እንደሚቸር ገልጧል። .
የግል መከላከያ ቁሳቁሶችንና ፈጣን አንቲጂን መመርመሪያዎችን እስከ ዲሴምበር 31 ለአረጋውያን ክብካቤ መኖሪያ ቤቶች ለማቅረብ ከውሳኔ ላይ ደርሷል።

የአውስትራሊያ የጤናና ደኅንነት ተቋም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሰውነት አካላት ልገሳና የሰውነት አካላት ነቅሎ ተከላ እንቅስቃሴዎች ላይ በመላ አገሪቱ በእጅጉ ተፅዕኖ ማሳደሩን አመልክቷል።

በ2020 አካል ለጋሽ ሆነው ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች ወደ ሕሙማን የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ተግባር በ2019 በ18 ፐርሰንት እንደቀነሰና የ2021 ከ2020 ጋር ሲነፃፀርም በተጨማሪ 6.8 ፐርሰንት ዝቅ ማለቱን ገልጧል።
የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ከዳግም ኮቪድ-19 አገገሙ። አዳችም ምልክት ያልታየባቸው በመሆኑም እሑድ ዕለት ተገልለው ከቆዩበት ወጥተዋል።

የሉላዊ ኮቪድ -19 ተጠቂዎች ቁጥር በዘጠኝ ፐርሰንት እንዲሁም ሞት በ15 ፐርሰንት መቀነሱን የዓለም ጤና ድርጅት በየሳምንቱ በሚያወጣው ሪፖርቱ ኦገስት 21 አስታውቋል።

በሉል አቀፍ ደረጃ ጃፓን፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጀርመንና ሩስያ በኮቪድ ተጠቂዎች ቁጥር ከፍተኛውን ሥፍራ ያዘዋል።

የኮቪድ-19 መመርመሪያ ክሊኒኮችን ፈልገው ያግኙ።

Register your RAT results here, if you're positive

Here is some help understanding

Read all COVID-19 information in your language on the

Share
Published 25 August 2022 7:24pm
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS


Share this with family and friends