ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አመሻሽ ላይ የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ውይይትን ተከትሎ አውስትራሊያ የዘለቀውን አዲሱና በጣሙን ተዛማች የሆነው ኦሚክሮን ቫይረስ በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎች አስመልክቶ ክለሳ ለማድረግ የፀጥታ ስብሰባ ያካሂዳሉ።
ከደቡብ አፍሪካ ወደ አውስትራሊያ የገቡ ሁለት መንገደኞች በአዲሱ ቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። የአውስትራሊያ ዜግነት የሌላቸው ዘጠኝ የደቡባዊ አፍሪካ አገራት መንገደኞች ወደ አውስትራሊያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።
የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የፌዴራል መንግሥቱ የሕክምና ባለሙያዎችን ምክረ ሃሳቦች አድምጦ እንደ አስፈላጊነቱ በጉዞ እገዳዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል። አውስትራሊያ ከረቡዕ ዲሲምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፣ ባለሙያ ሠራተኞችና ባለቪዛዎች ድንበሮቿን ክፍት አድርጋለች።
በተጨማሪም መንግሥት የአውስትራሊያ ክትባት አማካሪ ቡድን ከአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት መከተቢያ ጊዜን እንዲከልስ በመንግሥት በኩል ጥያቄ ቀርቧል። በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ ዙር የማጠንከሪያ ክትባትን ለመወጋት ሁለተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለስድስት ወራት መጠበቅን ግድ ይላል።
የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮንን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ በ | | | | | አውጥቷል።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,007 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 150 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሶስቱ በአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሳይጠቁ እንዳልቀረ ተገምቷል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤