የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ በግሬተር ሲድኒ የተጣለው ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር ተራዘመ ፤ ኮሮናቫይረስ በሪጅናል ቪክቶሪያ መሰራጨቱ ተነገር

ይህ በአውስትራሊያ በኦገስት 20.2021 የተሻሻለ የእርስዎ የኮሮናቫይርስ መረጃ ነው ።

Health workers and Police officers are seen at a unit block under lockdown, in Campsie, south west of Sydney, Friday, August 20, 2021. (AAP Image/Dan Himbrechts) NO ARCHIVING

Health workers and Police officers are seen at a unit block under lockdown, in Campsie, south west of Sydney, Friday, August 20, 2021. Source: AAP Image/Dan Himbrechts

  •  ኒው ሳውዝ ዌይልስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በስፋት ታይቶባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ላይ ተጨማሪ ገደቦችን አስቀመጠች
  • በቪክቶሪያ ምንጩ ያልታወቀውን አንድ ኮሮናቫይረስ ፍለጋ ቀጠለ
  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 12 ሰዎች በኮሮና ቨይረስ ተጠቁ


ኒው ሳውዝ ዌይልስ 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 644 ነዋሪዎቿ በማህበረሰብ ውስጥ ባለ የኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ፤ከነዚህ ውስጥም 41 ያህሉ ቫይረሱን በሚያስተላልፉበት ወቅት በማህበረሰቡ ውስጥ ነበሩ፡፡በተያያዘም አራት ሰዎችም ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ሁሉም የመጀመሪያውን ከትባት መውሰዳቸው ተገልጥጿል ፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በስፋት ታይቶባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች በሚኖሩ ነዋሪዎች እና የንግድ ተቋማት ላይ ተጨማሪ ህጎች    ከሰኞ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 12 ፡ 01  ጀምሮ በተግባር የሚውል ይሆናል፡፡ ይህ የሰአት እላፊ ገደብንም የሚያካትት ሲሆን ገደቡም ከምሽት 9፡00 እስከ ንጋት 5፡00 የሚዘልቅ ይሆናል ፡፡የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ከአንድ ሰአት በላይ ማድረግ አይቻልም ፡፡

በግሬተር ሲድኒ አካባቢ የተጣለው ገደብ እስከ  ሴፕቴምበር 30 ድረስ ተራዝሟል ፡፡

ለክትባትዎ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ቀጠሮን የያዙ ፦  .

ቪክቶሪያ

በቪክቶሪያ 57 ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ ባለ የኮሮናቫይረስ ስርጭት የተያዙ ሲሆን ፤ ከነዚህ ውስጥ ስድስቱ የተያዙት ቀድሞ ከተከሰተው ወረርሽኝ ባልተያያዝ መንገድ ሲሆን ፤  ሰላሳ የሚሆኑትም ቫይረሱን በሚያስተላልፉበት ወቅት በማህበረሰቡ ውስጥ ነበሩ፡፡

በቪክቶሪያ ሪጅናል ሼፐርተን የታየውን አንድ የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ የጤና ባለስልጣናቱ ክትትል እንዲደረግ ትእዛዝን አውጥተዋል፡፡

ቫይረሱ በስፋት ታይቶባቸዋል የተባሉትን አካባቢዎች በተመለከተ     እና

የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ሊንኮቹን ይጫኑ 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ  12 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የአንዱን ምንጭ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡ በአሁን ሰአት በካንብራ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር  94 ደርሷል ፡፤

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘም  አንድ ሰው ሆስፒታል የገባ ሲሆን ፤ ከ250 በላይ አካባቢዎች የህዝብ ትራንስፖርቶች ፤ የፈጣን ምግብ መሸጫዎች እና ሙአለ ህጻናትን ጨመሮ ለኮቪድ መጋለጣቸው ታውቋል ፡፡

ያለፉት 24 ሰዓታትበአውስትራሊያዙሪያ

  • ኖርዘርን ቴሪሮሪ እና ኩዊንስላንድ በማህበረስብ ውስጥ የተላለፈ ምንም የኮሮናቫይረስ አልታየባቸውም
  • ደቡብ አውስትራሊያ ጠረፎቿን ለሰሜን እና ሪጅናል ኩዊንስላንድ እንዲሁም ለኖርዘን ቴሪቶሪ ክፍት አድርጋለች ፡፡
ወሸባ፣ጉዞ፣የክሊኒክምርመራናየወረርሽኝአደጋክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ACT  and 
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

 
 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 

alc covid mental health
Source: ALC


 


Share
Published 20 August 2021 5:43pm
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends