- በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የኮቪድ-19 መመርመሪያ ወጪ ለንግድና ተቋማትና ከሥራ ጋር ለተያያዘ ተግባር ለሚጠቀሙ ግለሰቦች የግብር ቅናሽ ውስጥ ተካታች እንደሚሆን ገለጡ። በድንጋጌው መሠረት ንግዶችና ግለሰቦች የፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ ወጪዎቻቸውን ከጁላይ 1, 2021 አንስተው በግብር ተመላሽ ጥያቄያቸው ውስጥ ማካተት ይችላሉ።
- አጣዳፊ ያልሆኑ ቀዶ ሕክምናዎች ከዛሬ ጀምሮ በተወሰኑ ክፍለ አገራት ግብር ላይ መዋል ይጀምራሉ። የቪክቶሪያ የግልና የቀን ማዕከላት ግልጋሎቶቻቸውን ከ50 ፐርሰንት ባላለፈ አቅማቸው የሚያካሂዱ ሲሆን፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የተወሰኑ የሕዝብ ሆስፒታል ሕሙማን ገሚሶች በግል ገሚሶች በአክባቢ የሕዝብ ሆስፒታሎች ውስጥ የቀዶ ሕክምና ግልጋሎቶችን ያገኛሉ።
- የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች በተወሰኑ የኩነት ሥፍራዎች check-in app መጠቀም ግድ እንዳይሰኙ ተደርጓል። ይሁንና በአያሌ ሥፍራዎች የክትባት ማረጋጋጫ ማቅረብ ግድ ይላል። መንግሥት ባለፈው ሳምንት ኦሚክሮን ኩዊንስላንድ ውስጥ የመስፋፋት ጫፍ ላይ መድረሱን ገልጧል።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪም በበኩሉ ከዓርብ 11.59pm ጀምሮ በተወሰኑ ሥፍራዎች ግዴታ የነበረውን QR code check-ins መጠቀምን አስቀርቷል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ባለፈው ረጅም ወረርሽኝን ወቅት ልጆቻቸውን ቤት ውስጥ ሲያስተምሩ የነበሩ ወላጆች ከመንግሥት የሽርሽር ድጎማ እንደሚያገለግሉ ፕሪሚየር ዶሜኒክ ፔሮቴይ አስታወቁ። በዚህም መሠረት መሥፈርቱን ከሚያሟሉ የአንድ ቤት ነዋሪዎች አንድ ግለሰብ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ኦክቶበር መጨረሻ ለማረፊያ ቤት መከራያ ወይም ለመዝናኛ የሚያውሉ አምስት ባለ $50 ቫውቸሮች ይታደላቸዋል።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 7,437 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,099 ሕመማን 137 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 8,275 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 7 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 638 ሕመማን 72 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 4,701 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 9 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 663 ሕመማን 43 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ታዝማኒያ 443 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ 15 ሕመማን ሆስፒታል ይገኛሉ።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ