- ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑዕ ሕመምተኞች ቁጥር እየናረ ነው።
- ዛሬ በሚካሔደው ብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ላይ የተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ፣ ክተባና አቅርቦቶች ጉዳይ ይመከራል ተብሎ ይጠበቃል።
- 33.4 ፐርሰንት ያህል ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ያሉ ልጆች የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ ክትባት ተከትበዋል።
- የሶስተኛ ዙር ክትባት ቀነ ቀጠሮዎችን አስይዘው የሚቀሩ ነዋሪዎችን አስመልክቶ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ማሳሰቢያ ሰጡ።
- የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ የሙሉ ክትባት ደረጃን ዕውን ማድረግ እንዲያስችል ብሔራዊ ካቢኔው የሶስተኛ ዙር ክትባት ከተባን ከግዴታ ጋር ሊያይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ።
- በአገር አቀፍ ደረጃ 59 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን አጡ።
- 23 የሮያል አውስትራሊያ ባሕር ኃይል አደላይድ የጦር መርከበኞች በኮቪድ 19 መያዝ ጋር ተያይዞ ለቶንጋ 'ንኪኪ አልባ' የእርዳታ አቅርቦት ተደረገ።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 17,316 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ29 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,722 ሕመማን 181ዱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 13,755 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 15 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,057 ሕመማን 117ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 11,600 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 15 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 829 ሕመማን 48 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ደቡብ አውስትራሊያ 1,953 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 288 ሕመማን 27 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሆስፒታል ሕሙማን 73 ሲደርስ አራት በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ