- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 40 ፐርሰንት ነዋሪዎች የሁለተኛ ዙር ክትባት ተከትበዋል
- ቪክቶሪያ ተጋላጭ ለሆኑ ማኅበረሰባት የድጋፍ እቅዷን አስታወቀች
- 15 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቁ
- ኩዊንስላንድ አንድ ሰው በቫይረስ የተያዘባት መሆኑን አስመዘገበች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,485 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከአንድ ሺህ በላይ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ፤ 175ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ውስጥ ሲገኙ 72ቱ የመተፈንሻ ቁሶች ተገጥሞላቸዋል።
ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ውስጥ 40 ፐርሰንቱ የሁለተኛ ዙር 73 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል። እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የክትባት ደረጃ 80 ፐርሰንት ሲደርስ ኒው ሳውዝ ዌይልስ "ዳግም ክፍለ አገር አቀፍ ገደቦች አይጣልባትም" ብለዋል። ሆኖም በሚቀጥሉት አሥራ አራት ቀናት በቫይረስ የሚጠቁ ሰዎች ቁትር እንደሚያሻቅብ አስጠንቅቀዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 183 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 110ሩ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 15 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ 13ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። ስድስቱ በወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።
- ኩዊንስላንድ ውስጥ አንዲት እናት በቫይረስ ተዛለች፤ ልጇ በትናትናው ዕለት በቫይረስ ተጠቅቶ ነበር።
- የምዕራብ አውስራሊያ እንደራሴ የክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ ነዋሪዎች የክትባት መጠን 80 ፐርሰንት ሳይደርስ የክፍለ አገሩ ወሰን ክፍት የሚሆንበት ቀን እንደማያስታውቁ ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤