የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ከዛሬ 6pm ጀምሮ ሊዝሞር እና አልበሪ ላይ ለሰባት ቀናት የሚቆይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጣለ

*** ቪክቶሪያ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች

COVID-19 update

The regional LGAs of Lismore and Albury will go into a seven-day lockdown from 6pm tonight, 16 September 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 12 የአሳሳቢ አካባቢ መንግሥታት ክፍለ ከተሞች ከተጣለባቸው ገደብ ወጡ
  • ቪክቶሪያ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮቪድ-19 ድጎማዎችን ጨመረች
  • ኩዊንስላንድ አንድ ወሸባ ውስጥ ያለ ግለሰብ በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,351 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሕይወታቸውን ካጡት 12 ሰዎች ውስጥ 10ሩ ያልተከተቡ ናቸው።

በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ሳቢያ ከዛሬ 6pm ጀምሮ ሊዝሞር እና አልበሪ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ገደብ ተጥሎባቸዋል።  

ከዛሬ 1 pm ጀምሮ Bega Valley, Blayney, Bogan, Cabonne, Dungog, Forbes, Muswellbrook, Narrabri, Parkes, Singleton Snowy Monaro እና Upper Hunter Shire ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ይረግባሉ

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 514 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። በጠቅላላው 4,370 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል።

ቪክቶሪያ ውስጥ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት ይደርሳል። ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉ የተወሰኑ ገደቦች ከዓርብ እኩለ ለሊት ጀምሮ ይረግባሉ  

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች በቡድን ከአምስት ሳይበልጡ ከቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ። ከትባት ያልተከተቡ ወይም የመጀመሪያ ዙር ክትባት ብቻ የተከተቡ ሰዎች ከሁለት በላይ መሰባሰብ አይፈቀድላቸውም። ለሸመታና አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ነዋሪዎች ቀደም ሲል ከነበረው የ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደብ አልፈው ከቤታቸው እስከ 10 ኪሎ ሜትር ርቀው መሔድ  ይችላሉ።


በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

15 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።  

የጋራ ብልጽና እና የአውስትራሊያ ካፒታል መንግሥት ለቱሪዝም፣ የመኝታ ግልጋሎት ሰጪዎች፣ ሥነ ጥበብ፣ ኩነቶችና መስተንግዶ ዘርፎች የኮቪድ-19 የንግድ ድጎማዎችን ጨምረው ለመስጠት ተስማምተዋል። ድጎማ ለማግኘት ማመልከት ካሹና ተጨማሪ መረጃን ከፈለጉ ይህን ይጫኑ 

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ .                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የሰሜናዊ ቴሪቶሪ በወርኃ ኖቬምበር መጀመሪያ 80 ፐርሰንት ያህል ነዋሪዎችን ሙሉ ክትባት ለመከተብ አልሟል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 16 September 2021 2:40pm
Updated 16 September 2021 2:44pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends