- የሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ግራፍተን ነዋሪዎች ምርመራ እንዲያካሂዱ ተጠየቁ
- ቪክቶሪያ ውስጥ እስካሁን 6,666 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ላይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ከተጣለ ሰባተኛ ሳምንቱን አስቆጠረ
- ኩዊንስላንድ አንድ ወሸባ ውስጥ ያለ ግለሰብ በቫይረስ መያዙን አስመዘገበች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,063 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ኦሬንጅ እና ግሌን ኢነስ የአካባቢ መንግሥት አካባቢዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገድብ ዛሬ ያበቃል። ናሮማይን ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ ሴፕቴምበር 25 ይነሳል።
በሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ግራፍተን የቁሻሻ ፍሳሽ ውስጥ የቫይረስ ናሙናዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እንዲመረመሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 766 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የሕክምና ፈቃድ ከሌላቸው በፊት ሙዋዕለ ሕፃናትን ጨምሮ ከ100,000 በላይ አስተማሪዎች ከኦክቶበር 18 በፊት ቢያንስ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ከኖቬምበር 29 በፊት ሙሉ ክትባት እንዲከተቡ ግድ ተብለዋል።
ሙሉ ክትባት የተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ከሴፕቴምበር 30 በፊት ወደ መኖሪያ ቀዬአቸው መመለስ እንዲችሉ ፈቃድ ተሰጠ። እንዲሁም፤ ከ72 ሰዓታት በላይ ያልቆየ የኮቪድ-19 ነፃ መሆን ማስረጃና የ14 ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ መግባት ይጠበቅባቸዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 16 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች፤ በተቅላላው 674 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ 12 እስከ 59 ያሉ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ካሉ የመድኃኒት ቤቶች ዘንድ ሞደርና ክትባትን መከተብ ይችላሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የፌዴራል ቱሪዝም ሚኒስትር ዳን ቲሃን መንግሥት የክትባት ፓስፖርትን አካትቶ አስገዳጅ የሆቴል ወሸባ አልባ ዓለም አቀፍ ጉዞን "ቢያንስ ለገና" አምቺ አሠራሮችን ግብር ላይ ለማዋል እየተሰናዳ መሆኑን ገለጡ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤