የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የአገር ውስጥ ተጓዦች በክፍለ አገር መንግሥታት ክሊኒኮች ለሚያደርጉት የኮቪድ-19 ምርመራ ክፍያ መፈጸም አንደማይጠበቅባቸው አስታወቁ። ቀደም ሲል የአገር ውስጥ መንገደኞች ለአንድ ምርመራ $150 መክፈል ይኖርባቸው ወይም አይኖርባቸው እንደሁ ብዥታ ፈጥሮ ነበር።
ኩዊንስላንድ፣ ምዕራብ አውስትራሊያና ደቡብ አውስትራሊያ መንገደኞች ከግዛታቸው ከመዝለቃቸው በፊት 72 ሰዓታት ቀደም ብለው አፍንጫና ጉሮሮን ያካተተ የቫይረስ ምርመራን PCR ውጤት እንዲያቀርቡ ግድ ይላሉ።
በሚቀጥለው ዓመት ከጃኑዋሪ 17 ጀምሮ የኒውዝላንድ ዜጎችና ሌሎችም የጉዞ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መንገደኞች ወደ ኒውዝላንድ መጓዝ ይችላሉ። የሆቴል ወሸባ መግባትም አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ለሰባት ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ መግባት ይጠበቅባቸዋል።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,196 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 248 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ 11 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ኩዊንስላንድ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ አልተመዘገበም።
በቫይረስ ተይዘዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤