የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ሜልበርን ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ ለአንድ ሳምንት ተራዘመ

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 344 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ

COVID-19 update

Health staff monitor people after receiving a COVID-19 vaccination at the Royal Exhibition Building in Melbourne, Tuesday, August 10, 2021. Source: AAP

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዳቦ ሪጅን ገደብ ተጣለበት
  • ቪክቶሪያ ውስጥ አምስት የቫይረስ ምንጮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው
  • ኬይንስ ላይ የተጣለው ገደብ ተነሳ

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 20 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። አምስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።  

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ሜልበርን ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እስከ ሐሙስ ኦገስት 19 መራዘሙን አስታወቁ። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  .

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 344 ሰዎች በቫይረስ የተያዙባት ሲሆን 65 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። አንድ ዕድሜያቸው በ90ዎቹ ያሉና አንድ በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ግለሰብ በኮቪድ-19 ተጠቅተው ሕይወታቸው አልፏል። ሁለቱም ክትባት ያልተከተቡ ነበሩ። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዳቦ ሪጂን ላይ ከዛሬ ረቡዕ ኦገስት 11 ከቀትር በኋላ 1pm ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ገደብ ተጥሏል። ለገደቡ መጣል አስባብ የሆነውም ሁለት ግለሰቦች በቫይረስ ተጠቅተው በመገኘታቸው ነው።   

ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ኬሪ ቻንት እንደገለጡት በፅኑዕ ህሙማን ክፍል በመታከም ካሉት 62 ሰዎች ውስጥ 57ቱ ያልተከተቡ ሲሆን አምስቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ናቸው። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሁሉም ቀደም ሲል ቫይረሱ ተዛምቶባቸው ያሉ ሥፍራዎች ነዋሪዎችና ወሸባ ገብተው የሚገኙ ናቸው። 

ኬይንስ እና ያራባህ ላይ ተጥለው የነበሩት ገደቦች ከዛሬ 4 pm ጀምሮ ይረግባሉ፤ የተወሰኑ ገደቦች ጸንተው ይቀጥላሉ .

ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸውና ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ለክትባት እንዲመዘገቡ አሳስበዋል። 

የክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ .

ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 11 August 2021 1:23pm
Presented by kassahun Seboqa
Source: SBS

Share this with family and friends