- የቪክቶሪያ ገደብ በላላበት ዕለት 16 ሰዎች በኮቪድ-19 ሕይወታቸው አለፈ፤ 2,189 በቫይረስ ተጠቁ።
- ኳንታስ የዓለም አቀፍ በረራ ዕቅዱን አሻሻለ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን መንግሥት ከሲንጋፖር ጋር የመንገድኞች በረራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቡን ጠቆሙ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 2,189 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 16 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሜልበርን በዓለም ረጅም ከተባለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ቆይታ ተላቅቃለች።
ሙሉ ክትባት የተከተቡ የከፍለ አገሪቱ ነዋሪዎች ቁጥር ቀደም ብሎ ታስቦ ከነበረው ኖቬምበር 5 በአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ኦክቶበር 30 ላይ 80 ፐርሰንት ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ተከትበው ከባሕር ማዶ ወደ ቪክቶሪያ የሚመጡ አውስትራሊያውያን ወሸባ እንዳይገቡ መወሰኑን አስታወቀዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 345 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ኳንታስ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሠራተኞቹን ወደ ሥራ መልሶ የዓለም አቀፍ በረራውን ለመጨመር ማቀዱን ባስታወቀበት በዛሬው ዕለት፤ ሲድኒ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙት እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ ኒው ሳውዝ ዌይልስ "የመልሶ መቋቋም ማኮብኮቢያ" ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል።
በሥፍራው ተገኝተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም በበኩላቸው አውስትራሊያውያን ወደ ሲንጋፖር መጓዝ እንዲችሉ በመጪው ሳምንት ከስምምነት ላይ ለመድረስ የመቋጫ ንግግር ላይ መኮኑን አመላክተዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 13 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆነ 84 ፐርሰንት ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም በቫይረስ የተጠቃ ሰው አልተመዘገበም፤ ይሁንና የሎጋን ከትባት መጠን አሳሳቢ ሆኗል። በነገው ዕለት በ100 የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢዎች ውስጥ መጠነ ሰፊ 'የልዕለ ቅዳሜ' ክትባት ይካሄዳል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤