- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 90 ፐርሰንት የሚያልፍባትን የዛሬዋን ቀን 'በዕለተ ምዕራፍነት' ጠርተዋል።
- የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር የሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ስፓይክቫክስ SPIKEVAX ዕድሜያቸው ከ6-11 ላሉ ልጆች እንዲሰጥ ይሁንታ ቸረ።
- የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼ ተያያዥነት የሌለው የቫይረስ ክስተት ጎልድ ኮስት ላይ ከተገኘ ተጨማሪ ገደቦች ሊጣሉ እንደሚችሉ አሳሳቡ
- አውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ ለ33 ነዋሪዎች በቫይረስ መጠቃት ምንጩ ከአንድ ሕጋዊ ያልሆነ የሃለዊን ፓርቲ ጋር ተያይዟል
- 80 ፐርሰንት የታዝማኒያ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል
- ፊጂ ከዲሴምበር 1 ጀምሮ ድንበሮቿን ለአውስትራሊያ ከት የምታደርግ ሲሆን፤ የፊጂ ፓስፖርት ባለቤት፣ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ባለ ይለፍ ፈቃድና ተመላሽ ነዋሪዎች ወደ ፊጂ መጓዝ ይችላሉ
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,313 በቫይረስ ሲጠቁ፤ አራት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 261 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
ኩዊንስላንድ ውስት ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ አንደኛው አሁን ተከስቶ ካለው የቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያያዥ አይደለም።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤