- ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የሁለተኛ ዙር ክትባት ከተከቡ ስድስት ወራት ለሆናቸው ነዋሪዎች የሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ፕሮግራም ከዛሬ ጀምሮ በይፋ መጀመሩን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታወቀ።
- የሜልበርን ከተማ ላይ ዳግም የደመቀ ሕይወት ለመዝራት ለመመገቢያ የሚውል የ$5 ሚሊየን እደላን አካትቶ $44 ሚሊየን ዶላርስ ተመድቧል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ በቤት ውስጥ የጎብኚዎች ቁጥር ላይና በውጪም በቡድን የመሰባሰብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ሙሉ በሙሉ ተነስተዋል።
- የቪክቶሪያ መንግሥት ለትምህርት ቤቶች ነፃ የቤት ውስጥ መመርመሪያ እያደለ ነው።
በኮቪድ-19 የተያዙ፤
- ቪክቶሪያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 1,126 ሰዎች በቫይረስ ሲተቁ አምስት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ 187 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቀታቸውንና ሰባት ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጋቸውን አስመዘገበች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤