ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ21 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ

*** ደቡብ አውስትራሊያ የብሔራዊ ካቢኔውን አዲስ "የቅርብ ንኪኪ" ትርጓሜ ውድቅ አደረገች

COVID-19 update

Prime Minister Scott Morrison holds a National Cabinet meeting in Canberra, 30 December. Source: AAP

  • የክፍለ አገራት መሪዎች በትናንትናው ዕለት በ ‘’ ትርጓሜ በትናንትናው ዕለት ከስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ፣ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪና ኩዊንስላንድ ከዕኩለ ለሊት ጀምሮ ግብር ላይ ውሏል

  • ታዝማኒያ አዲሱን የ'ቅርብ ንኪኪ' ትርጓሜ ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ ግብር ላይ የምታውል ሲሆን፤ ምዕራብ አውስትራሊያና ኖርዘርን ቴሪቶሪ በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ መች ግብር ላይ እንደሚያውሉት ያስታውቃሉ። ደቡብ አውስትራሊያ አዲሱን ድንጋጌ ውድቅ አድርጋለች። 

  • በአዲሱ ትርጓሜ መሠረት 'የቅርብ ንኪኪ' ማለት በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር፤ በአንድ ቤት ነዋሪ ከሆኑ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በኮቪድ-19 መያዙ ከተረጋገጠ ቤተኛ ጋር፣ ከቤት ውጪ ባሉ 'መኖሪያ ቤት መሰል' ወይም የክብካቤ ተቋም ውስጥ ከአራት ሰዓታት በላይ አብሮ ያሳለፈ ግለሰብ ነው

  • ይህንኑ የትናንት የጋራ ስምምነት አዘል ትርጓሜ ግና የደቡብ አውስትራሊያ ዋና የሕዝብ ጤና መኮንን ውድቅ በማድረግ፤ የቅርብ ንኪኪ ማለት ማንኛውም በቫይረስ ከተጠቃ ግለሰብ ጋር ከ15 ደቂቃ በላይ ጊዜን ያሳለፈ ግለሰብ ማለት እንደሆነ ገልጠዋል

  • በአብዛኛዎቹ ክፍለ አገራት የኮቪድ-19 ተጠቂዎችና የቅርብ ንኪኪዎች ለሰባት ቀናት ራሳቸውን እንዲያገልሉና በስድስተኛው ቀን ፈጣን ምርመራ እንዲያካሂዱ የሚያደርጉ ሲሆን፤ ደቡብ አውስትራሊያ ግና ራስን አግልሎ የመቆያ ጊዜ 10 ቀናት እንዲሆኑ ወስናለች

  • ታዝማኒያ ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ ወደ ግዛቷ በሚዘልቁ መንገደኞች ላይ ጥላ የነበረውን የPCR ምርመራ ድንጋጌ አንስታለች

  • ደቡብ አውስራሊያ ውስጥ ገና ሁለት ዓመት ሳይሞላው በኮቪድ 19 ተጠቅቶ ለሕልፈት ሕይወት የበቃው ሕፃን አሟሟት ምርመራ ውጤት እስካሁን ይፋ አልሆነም

  • ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ያለ የአውስትራሊያ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከታቢዎች ደረጃ 90 ፐርሰንት ደረሰ

  • ፈጣን ምርመራ ማካሔጃ RAT ዋጋ አሻቅቧል፤ አንድ የሲድኒ መድኃኒት ቤት አንድ ነጠላ መመርመሪያን በ$25 እየሸጠ ነው

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 21,151  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 5,919 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 3,118፣ ታዝማኒያ 137 ሰዎች ተጠቅቶባቸዋል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ .

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  

 

 


Share
Published 31 December 2021 2:42pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends