የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የአውስትራሊያ መዲናና ሲድኒ ላይ አዲስ ገደቦች ተጣሉ

*** የኩዊንስላንድ እንደራሴ ፓለሼ ደቡብ አውስትራሊያውያን ወደ ኩዊንስላንድ በአየር መምጣት እንደሚችሉ ሲያስታውቁ የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች ወደ ኒው ሳዝ ዌይልስ ወሰን ተሻግረው እንዳይዘልቁ አስጠንቅቀዋል።

COVID-19 update

The ACT lockdown is a result of a positive COVID-19 case in the Territory who has been infectious whilst in the community, and positive wastewater detections. Source: Getty

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ተጨማሪ ገደቦች እየጠበቁ ነው
  • ለሜልበርን ንግዶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚሰጥ ተገለጠ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዛሬ 5pm ጀምሮ ገደብ ተጣለባት
  • ደቡብ አውስትራሊያውያን ወደ ኩዊንስላንድ በአውሮፕላን መሔድ ይችላሉ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 345 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 60 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። ሁለት ዕድሜያቸው 90ዎቹ ውስጥ ያሉ አረጋውያን ሕይወትም በኮቪድ-19 አልፏል።

Bogan, Bourke, Brewarrina, Coonamble, Gilgandra, Narromine, Walgett and Warren አካባቢዎች ገደብ ተጥሎባቸዋል። ገደብ የተጣለባቸውን የኒው ሳውዝ ዌይልስ አካባቢዎች ዝርዝር ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  .

Bayside, Burwood እና Strathfield ከ5pm ጀምሮ ተጨማሪ የኮቪድ-19 ገደቦች ተጥሎባቸዋል። ይህም ሲድኒ አካባቢ ገደብ የተጣለባቸውን አካባቢዎች 12 አድርሷቸዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 21 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። አራቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 

የሥራ፣ ፈጠራና ንግድ ሚኒስትር ማርቲን ፓኩላ በሁለተኛው ሳምንት ገደብ ጉዳት ለሚያገኛቸው ከ100,000 በላይ የሜልበር ንግዶች ተጨማሪ እገዛዎች እንደሚቸሩ አስታውቀዋል።

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከአንድ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ በኮቪድ-19 የተጠቃ ሰው ተገኝቶባታል። በዚህም ሳቢያ ከዛሬ 5pm ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ገደብ ተጥሎባታል። .
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ 10 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሁሉም ቀደም ሲል ቫይረሱ ተዛምቶባቸው ያሉ ሥፍራዎች ነዋሪዎችና ወሸባ ገብተው የሚገኙ ናቸው። 
  • የኩዊንስላንድ እንደራሴ ፓለሼ ደቡብ አውስትራሊያውያን ወደ ኩዊንስላንድ በአየር መምጣት እንደሚችሉ ሲያስታውቁ የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች ወደ ኒው ሳዝ ዌይልስ ወሰን ተሻግረው እንዳይዘልቁ አስጠንቅቀዋል። 
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 12 August 2021 1:52pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends