የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ የሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ የኮቪድ-19 ክትባት የጊዜ ገደቡን ጠብቆ እንዲሰጥ ተወሰነ

*** የአፍሪካውያን-አውስትራሊያ ማኅበረሰብ መሪዎች መንግሥት የኦሚኮርን ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተቃወሙ

COVID-19 update

NSW Premier Dominic Perrottet: Indoor mask wearing is mandated Source: AAP

  • ሰሜን ቴሪቶሪ ውስጥ የመጀመሪያ የኮቪድ ሞት ተመዘገበ። እስካሁን ድረስ አውስትራሊያ ውስጥ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ሞት ስታስመዘግብ የቆየችው ኖርዘን ቴሪቶሪ ብቻ ነበረች።
  • የፌዴራል ጤና ሚኒስትር የብሔራዊ ፍኖተ ካርታ ላይ ለውጥ እንደማይደረግ አስታወቀ።
  • የአፍሪካውያን-አውስትራሊያ ማኅበረሰብ መሪዎች መንግሥት የኦሚኮርን ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተቃወሙ።
  • ምዕራብ አውስትራሊያ የደቡብ አውስትራሊያ ኮሮናቫይረስ ደረጃ ከ "ዝቅተኛ" ወደ "መካከለኛ" ከፍ በማለቱ መንገደኞች ወደ ግዛቷ እንዳይዘልቁ አገደች።
  • የብሔራዊ ክትባት ጠበብት ቡድን የሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ የኮቪድ ክትባት ከስድስት ወራት ጊዜው ዝቅ እንዳይል ወሰነ።
  • የፌዴራል መንግሥቱ ለኮቪድ መከላከያ የሚውል ተጨማሪ $540 ሚሊየን መደበ። 
  • ታዝማኒያ ከዲሴምበር 15 ጀምሮ የጉዞ ድንጋጌዎቿን ለወጠች 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,188 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 337 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አራት፣ ኖርዘርን ቴሪቶሪ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘውባቸዋል።  

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


 

 


Share
Published 3 December 2021 5:46pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends