- ከነገ ጀምሮ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የተወሰኑ ገደቮች ይረግባሉ
- ቪክቶሪያ ውስጥ 7,000 የፋይዘር ከትባት ቀጠሮዎች ክፍት ሆነው ተከታቢዎችን እየጠበቁ ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 15 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲጠቁ ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረስ አልተያዘም
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,262 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ በ12ቱ የስጋት አካባቢ መንግሥት ነዋሪዎችን ስያካትት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ በ12ቱ የስጋት አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑና ሙሉ ክትባት የተከተቡ አብረዋቸው በአንድ ቤት ከሚኖሩ የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር በመሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ለሽርሽር ወይም ለመዝናናት እንዲሁም ላልተወሰነ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከቤታቸው መውጣት ይችላሉ።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ የመጀመሪያ ዙር ተከታቢዎች ቁጥር 78 ፐርሰንት፣ ሙሉ ክትባት የተከተቡቱ 45.58 ሲደርስ ዓለም አቀፍ ድንበሮቿን ለመክፈት መወጠኗን አስታወቁ።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 334 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ በመጪው ሳምንት 7,000 የመጀመሪያ ዙር ፋይዘር ክትባት በመንግሥት ስር ባሉ ክሊኒኮች ለተከታቢዎች እንደሚዳረሱ አስታወቁ።
ቪክቶሪያ ውስጥ በስምንት ትምህርት ቤቶችና የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሂዩም፣ ዳንዲኖንግ እና ካሲ፤ እንዲሁም ቶርንበሪ የሚገኘውን የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሚል ፓርክ የሚገኘውን የሂንዱ መቅደስና ኒውፖርት የሚገኘውን መስጊድ ጨምሮ አዲስ የክትባት መከተቢያዎች ይከፈታሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አንድ ሚሊየን ተጨማሪ የሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ለማናቸውም ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በክትባትነት እንዲሰጥ ይሁንታ መቸሩን ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤