የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ እና ታዝማኒያ የቤት ውስጥ ወሸባ የሙከራ ዕቅዶቻቸውን አስታወቁ

***ቪክቶሪያ ከዕኩለ ለሊት በኋላ የተወሰኑ ገደቦቿን ታረግባለች

COVID-19 update

Doctor administers a Covid vaccine to 12 year old at a pop-up drive through vaccination clinic at Belmore Oval, in Sydney, Friday, September 17, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ እንደምታካሂድ አስታወቀች
  • ቪክቶሪያ ከዕኩለ ለሊት በኋላ የተወሰኑ ገደቦቿን ታረግባለች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ የአረጋውያን መጠወሪያ ክትባት ግዴታ ሆነ
  • ኩዊንስላንድ አንድ ወሸባ ያለ ሰው በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,284 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሕይወታቸውን ካጡት 12 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ወንዶች ዕድሜያቸው 20ዎቹ ውስጥ የነበረ ናቸው። ሶስቱ የዳቦ አረጋውያውያን መጠወሪያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን ሰባቱ አልተከተቡም። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን በTGA ተቀባይነት ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ለሰባት ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቁ። የመነሻ ሙከራው የሚከናወነው በ175 መንገደኞች ላይ ሲሆን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይጀመራል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 510 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

ከዛሬ እኩለ ለሊት አንስቶ ክትባት ያልተከተቡ ወይም የመጀመሪያ ዙር ብቻ የተከተቡ ነዋሪዎች አንድ ከመኖሪያቸው ውጪ ከሆነ ግለሰብ ጋር የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ሽርሽር መሄድ ይችላሉ። ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ከሁለት መኖሪያ ቤቶች ልጆቻቸው ሳይቆጠሩ እስከ አምስት ሆነው በቡድን የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ሽርሽር መሄድ ይፈቀድላቸዋል።  

ከገደቦች መውጫንና እስከ ኖቬምበር ተጥለው የሚቆዩ የገደብ ዓይነቶችን የሚያመላክተውን ፍኖተ ካርታ መንግሥት እሑድ ሴፕቴምበር 19 ይፋ ያደርጋል። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

30 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።  

ከዛሬ ጀምሮ ክትባት ያልተከተቡ የአረጋውያን መጠወሪያ ሠራተኞች የመጀመሪያ የኮቪድ-19 ክትባት እስካልተከተቡ ድረስ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዳይመለሱ የተደነገገው ድንጋጌ ግብር ላይ ውሏል። 

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ .                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

Share
Published 17 September 2021 3:12pm
Updated 17 September 2021 3:37pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends