የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሃንተር ቫሊ ላይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ጣለች

*** ኩዊንስላንድ እስከ ኦገስት 8 ጥላ ያለውን የኮሮናቫይረስ ገደብ በዕለቱ ያብቃ አያብቃ እርግጠኛ አይደለችም

COVID-19 update

Newcastle residents are tested at a drive through collection centre in Adamstown, Newcastle, Thursday, August 5, 2021. Source: AAP

  • ሃንተር ቫሊ ሪጅን ከዛሬ አመሻሽ 5 pm ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጣለበት
  • በዛሬው ዕለት ብሪስበን ውስጥ በቫይረስ የተጠቁት በሙሉ ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
  • ቪክቶሪያ ምንጩ ያልታወቀ ቫይረስ ተክስቷል፤ ተጨማሪ ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
  • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ የፋይዘር ክትባት ለኒው ሳዝ ዌይልስ መመደቡን አስታወቁ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 262 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውንና አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስመዘገበች። ለሕልፈተ ሕይወት ከተዳረጉት ውስጥ አራቱ ክትባት ያልተከተቡ ሲሆኑ አምስተኛው ሰው የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተበ ነበር።

ከዛሬ አመሻሽ 5 pm ጀምሮ እስከ 13 ኦገስት 12.01 am ድረስ በ Newcastle, Lake Macquarie, Maitland, Port Stephens, Singleton, Dungog, Muswellbrook እና Cessnock ላይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጥሏል። 

ዋና የጤና ኃላፊ ኬሪ ቻንት በ Armidale እና Dubbo አካባቢ የቫይረሱ መጠን እየጨመረ በመሆኑ ነዋሪዎች ምርመራ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ማንኛውም ነዋሪ ክትባት እንዲከተብ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት 16 ሰዎች በቫይረስ የተያዙ መሆናቸውንና በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች በመሉ ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።

ምክትል እንደራሴ ስቴቨን ማይልስ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 12ቱ የብሪስበን ነዋሪዎች ወሸባ ገብተው ያሉ መሆናቸውንና እስካሁን በቫይረሱ ተይዘው ያሉ ሰዎች ቁጥር 79 መድረሱን ገልጠዋል። እስከ ኦገስት 8 ተጥሎ ያለው ገደብ በዕለቱ ያብቃ አያብቃ በእርግጠኝነት አልተናገሩም። 

ስለ ኮሮናቫይረስ ተጨማሪ መረጃን በቋንቋዎ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ቪክቶሪያ ቫይረሱ ከየት እንዳገኛቸው በምርመራ ላይ ያለውን አንዲት መምህርት ጨምሮ በዛሬው ዕለት ስድስት ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት መሆኑን አስታወቀች።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ለኒው ሳውዝ ዌይልስ ተጨማሪ 180,000 የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት ኦገስት 16 እንደሚላክ ገለጡ።.
 


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 5 August 2021 2:51pm
Updated 5 August 2021 2:53pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends