- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እስከ ኖቬምበር 9 ተራዘመ
- ከ10 አንድ በቫይረስ የተጠቁ ቪክቶሪያን የሚገኙት ሼፐርተን ውስጥ ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ገደቦችን ከለሰች
- የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ፋይዘር ክትባት እንዲከተከቡ ይሁንታውን ቸረ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 882 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ብቫይረሱ ከተያሹት ውስጥ ከ80 ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። በ60ዎቹና በ90ዎቹ ዕድሜ የነበሩ ሁለት ወንዶችም ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ዕቅዶችን ይፋ አድርገዋል።:
- ከኦክቶበር 25 ጀምሮ - ከአጸደ ሕጻናት እስከ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች
- ከኖቬምበር 1 ጀምሮ - የ 2ኛ፣ 6ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች
- ከኖቬምበር 8 ጀምሮ - የ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች
ከኖቬምበር 8 ጀምሮ ለሁሉም የትምህርት ቤት ባልደረቦች ከትባት መከተብ ግዴታ ሲሆን፤ ከሴፕቴምበር 6 ጀምሮ እንዲከተቡ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 79 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 53ቱ ቀደም ብለው ከሚታወቁ ሥፍራዎች ሲሆኑ 26 ምንጫቸው ያልታወቀ ናቸው።
ከ 65,000 የሸፐርተን ነዋሪዎች ውስጥ 16,000 ያህሉ ራሳቸውን አግልለው ለመቆየት ግድ በመሰኘታቸው ምግብ አከፋፋዮች፣ ትላልቅ ሱቆችና መድኃኒት ቤቶች በሠራተኞች እጥረት ሳቢያ ተዘግተዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 21 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 221 ደርሷል።
ብሔራዊ መዲናይቱ ለንግድና ግልጋሎት ሰጪዎች ያካሄደችው ማሻሻያ ከዛሬ 11.59pm ጅርምሮ ግብር ላይ ይውላል
changes for retail business, waste drop-off services, gym and dance schools and real estate business
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ከዛሬ 4pm ጀምሮ የደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ የኮሮናቫይረስ ገደቦች በተጨማሪ ይላላሉ
- የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ፋይዘር ክትባት እንዲከተከቡ ይሁንታውን ቸረ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤