- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ኦቢሮን ነዋሪዎች ምርመራ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ
- የሪጂናል ቪክቶሪያ ባላራት ገደብ ሊያበቃ ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ይርክትባት ዒላማዋን ልትመታ ተቃርባለች
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ተጨማሪ በቀጥታ ሄዶ መከተቢያ ጣቢያ ተቋቋመ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,035 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ከኦክቶበር 6 አንስቶ ኒው ሳውዝ ዌይልስ የክትባት ማረጋገጫ ኧፕ ሙከራ ላይ ታውላለች። የ Service NSW app ነዋሪዎች 70 ፐርሰንት ሲደርስ ሙሉ ለሙሉ ግብር ላይ ይውላል።
በም ዕራባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ኦቢሮን የቁሻሻ ፍሳሽ ውስጥ የቫይረስ ናሙማዎች ተገኝተዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 628 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 57 ፐርሰንት የቫይረሱ ተጠቂዎች ከሰሜናዊ ሜልበርን ናቸው። የሶስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
ቪክቶሪያ 51,000 የአየር ማጣሪያዎችን ለእያንዳድንዱ የመንግሥት፣ በዝቅተኛ ክፍያ ለሚያስተምሩ የካቶሊክና የግል ትምህርት ቤቶች ለማስገጠም $190 ሚሊየን መመደቧን አስታወቀች። ይህም በአውስትራሊያ ውስጥ የመጀመሪያውና ትልቁ የአየር ማጣሪያ ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት መሆኑ ተገልጧል።
ባላራት ላይ ተጥሎ ያሉ ገደቦች ዛሬ እኩለ ለሊት ላይ ያበቃሉ። ሆኖም የፊት ጭምብልን ቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ማጥለቅን የመሰሉ የተወሰኑ ገደቦች ፀንተው ይቆያሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 17 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች፤ 11ዱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከታቢዎች 95 ፐርሰንት ለመድረስ ተቃርቧል። በአሁኑ ወቅት የክትባት መመዘኛን ከሚያሟሉ ነዋሪዎች ውስጥ ከ81 ፐርሰንት በላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 56 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ከሴፕቴምበር 22 ጀምሮ Boondall, Caboolture, Doomben, እና Kippa-Ring በቀጥታ ሄዶ መከተቢያ ጣቢያዎች ተከፍተዋል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤