የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ማሻቀብን ተከትለው ነዋሪዎች እንዲከተቡ ጥሪ እያቀረቡ ነው

*** የኩዊንስላንድ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ተጥሎ ያለውን ገደብ እሑድ ኦገስት 8 ይነሳል ብሎ ከወዲሁ በእርግጠኝነት ለመናገር ጊዜው ገና መሆኑን አመላከቱ

COVID-19 update

The media surround NSW Premier Gladys Berejiklian at a press conference to provide a COVID-19 update in Sydney. Friday, August 6, 2021. Source: AAP

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፅኑዕ ህሙማን ክብካቤ ክፍሎች ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ህሙማን ያልተከተቡ ናቸው
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማኅበረሰብ ተጋቦት ነው
  • በኩዊንስላንድ የክትባት ፕሮግራም በላይ የመድኅኒት ቤቶች ተሳታፊ ሆኑ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 292 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘውባታል፤ 48 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ነው። አንዲት ዕድሜያቸው በ60ዎቹ ውስጥ ያለ የደቡብ ምዕራብ ሲድኒ ነዋሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ቫይረሱ በብዛት በተዛመተበት ካንተርበሪ - ባንክስታውን አካባቢ የሕዝብ ጤና ድንጋጌዎች ጸንተው እንዲከበሩ የፖሊስ ኃይል እንዲጨምር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ኬሪ ቻንት ከ50 ፅኑዕ ህሙማን ውስጥ 44ቱ ያልተከተቡ ሲሆን የተቀሩት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ መሆናቸውን ገልጠዋል። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ማንኛውም ነዋሪ ክትባት እንዲከተብ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ትናንት ኦገስት 5 የተገለጡትን ሁለት በቫይረስ የተጠቁትን ጨምሮ በዛሬው ዕለት ስድስት ሰዎች በቫተስ መያዛቸውን ገልጣለች።

ሁሉም ስድስቱ ተጠቂዎች የተያዙት በዴልታ ሲሆን ወሸባ ገብተው የነበሩ አይደሉም። 

በትናንትናው ዕለት ለተጣለው ገደብ አስባብ የሆነው በሆብሰንስ ቤይ እና ማሪቢኖንግ ተከስቶ የተዛመተ ወረርሽኝ ነው። 

ቫይረሱ የተሰራጨባቸውን ሥፍራዎች ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት10 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን ገልጣለች። ሁሉም ገደብ ከተጣለባቸው አካባቢዎች ናቸው።

ከ330 በላይ የማሕበረሰብ መድኃኒት ቤቶች የኮቪድ 19 ክትባቶችን ለኩዊንስላንድ ነዋሪች እየሰጡ ነው  

የኩዊንስላንድ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ተጥሎ ያለውን ገደብ እሑድ ኦገስት 8 ይነሳል ብሎ ለማለት ጊዜው ገና መሆኑን ተናግረዋል።

 


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 6 August 2021 2:46pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends