የኮቪድ-19 መረጃ ፦ በኒው ሳውዝ ዌልስ “ በአገር አቀፍ ደርጃ የአደጋ ጊዜ ” አዋጅ ወጣ

NSW Premier Gladys Berejiklian and Chief Health Officer Dr Kerry Chant at a press conference to provide a COVID-19 update in Sydney.

NSW Premier Gladys Berejiklian and Chief Health Officer Dr Kerry Chant at a press conference to provide a COVID-19 update in Sydney. Source: AAP

ይህ በአውስትራሊያ ጁላይ 23፣ 2021 የተሻሽለ የእርስዎ የኮሮናቫይርስ መረጃ ነው ።

  • የኒው ሳውዝ ዌልስ ከፍተኛ የጤና ኦፊሰር ዶ/ር ኬሪ ቻንት  
“ በአገር አቀፍ ደርጃ የአደጋ ጊዜ ” አዋጅን ይፋ አድርገዋል

  • ፕሪምየር በርጂክሊያን ተጨማሪ  የፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት በደቡብ ም እራብ ሲድኒ እና ምእራብ ሲድኒ እንዲዳደረስ ጠይቀዋል፤
  • ቪክቶርያ ያስመዘገበችው ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም ፕሪምየር አንድሪውስ ገደቡ የሚነሳበትን ቀን ከመናገር ተቆጥበዋል ፤
  •  የፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት እድሜያቸው ከ 12-15 ላሉ ታዳጊ ህጻናት እንዲሰጥ ፍቃድ አገኘ፤
ኒው ሳውዝ ዌልስ

ኒው ሳውዝ ዌልስ 136 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ያስመዘገበች ሲሆን 53ቱ  በማህበረሰብ ውስጥ የተላለፉ ናቸው፤ በተጨማሪም የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ፡፡

በከምበርላንድ እና ብላክታውን አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፤ በጤና እና በድንገተኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከሚሰሩት በስተቀር ፤ የተቀሩት ለስራ ጉዳይ ከቤታቸው መውጣት አይችሉም  ፡፡ፈቃድ ያላቸውን የስራ መስኮች ዝርዝር ይመልከቱ ፦ .

ቪክቶርያ

ቪክቶርያ 14 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ያስመዘገበች ሲሆን አራቱ በማህበረሰብ ውስጥ የተላለፉ ናቸው፤ በአሁን ሰአት 158 የቫይረሱ ተጠቂዎች አሉ ፡፡

እንዲሁም ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸው 19000 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ይገኛሉ ፡፡

የቫይረሱ ስርጭት የታየበትን አካባቢዎች ካርታ  በተመለከተ የሚከተለው ሊንክ ይመልከቱ ፦

በአሁን ሰአት ያለው ገደብ እስከ ማክሰኞ ጁላይ 27 ክምሽቱ 11፡59 ድረስ እንደሚቆይ ይጠበቃል ፡፡

 ባለፉት 24 ሰአታት በመላው አውስትራሊያ 

  • ሳውዝ አውስትራሊያ ከ23, 000 የምርመራ ውጤት በማካሄድ አንድ የኮቪድ-19 ቫይረስን  አስመዝግባለች ፤
  • በብሪዝበን አንድ የኳንታስ የበረራ አስተናጋጅ ስድስት የአገር ውስጥ በረራዎችን ካስተናገደች በኋላ ቫይረሱ እንደተገኘባት ታውቋል ፤
  • እድሜያቸው ከ 40 አመት በታች የሆኑ ፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት እስከ ሴፕቴምበር እና ኦክቶበር ድረስ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ፤ በአንጻሩም የአውስትራሊያ ሜዲካል ህግ አውጪዎች ፋይዘር እድሚያቸው ከ 12-15  ላሉት ታዳጊዎች እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥቷል ፡፡ 
የኢድ አላድሀ በአል ( የመስእዋትነት በአል) ሰኞ ጁላይ 19 የሚጀምር ሲሆን በበአሉ የጸሎት ስነ ስራት ወቅትም ራስን እና ሊሎችን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን መውሰድ ይገባል ፦

  • ጸሎትን ከቤት ማድረግን ይምረጡ
  • በርካታ ሰዎች ከሚገኙበት ስፍራ ከመሄድ ይታቀቡ
  • የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ያድርጉ
  • የርስዎን የመስገጃ ምንጣፍ ይጠቀሙ  
ለይቶ ማቆያ ፤ ጉዞ፣ የመመርመሪያ ክሊኒኮች ፤ እና የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያ

የለይቶ ማቆያ እና የመመርመሪያ ክሊኒኮች የሚመሩት እና ተግባራቸውን የሚከውኑት  በክልሎቹ እና ግዛቶቹ መንግስታት ነው ፦

ACT  and 
ወደሌላ አገር መጓዝ ከፈለጉም እና ፈቃድን ለማግኛት ፤ በኦንላይን ፈቃድን  ይችላሉ      

ከአውስትራሊያ ውጪ እንዴት ማጓዝ እንደሚችሉ ተጨማሪ ማረጃን ማግኘት ይችላሉ ። ኣለማቀፍ በረራዎችን በተመለከተ ጊዜያዊ የሆኑ እርምጃዎች በየጊዜው በመንገስት የሚከለሱ እና የሚሻሻሉ ናቸው ስለሆነም ድረገጽን   ይመለከቱ ።

ዜናዎችን እና መረጃዎችን ከ 60 በላይ ቋንቋዎች ከ  ያግኙ

በሚኖሩበት ክልል እና ግዛት ያለውን ጠቃሚ መረጃ ከ   .  ያግኙ

የኮቪድ-19 ከትባትን በተመለከተ በቋንቋዎ መረጃን ከ  .  ያግኙ

የኒውሳውዝዊልስ የመድብለ ባህል ጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት ትርጉም መረጃዎችን  በተመለከተ ፦

የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የመመርመሪያ ክሊኒኮችን በተመለከተ ፦

 
 
የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያን መረጃ በተመለከተ፦

 
 
 

 

  

 

 


Share
Published 23 July 2021 10:47pm
Updated 23 July 2021 11:06pm
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS

Share this with family and friends