- በኒው ሳውዝ ዌይልስ አሁንም ድረስ በማኅበረሰብ ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ከፍተኛ ነው
- ኩዊንስላንድ ውስጥ በአብዛኛው በቫይረሱ የተያዙት ልጆች ናቸው
- ቪክቶሪያ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
- ደቡብ አውስትራሊያ ተጥለው የነበሩ የተወሰኑ ገደቦች ተነሱ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 207 በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ስዎችን አስመዝግባለች። በቫይረሱ ከተያዙት ውስት 50ዎቹ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። አንድ በ90ዎቹ ዕድሜ ያሉና የመጀመሪያ ዙር አስትራዜኒካ ኮቪድ -19 ክትባት የተከተቡ አረጋዊ ሕይወትም ሊቨርፑል ሆስፒታል ውስጥ አልፏል።
300 ያህል የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አባላት "እሽግ ምግቦችን በማደል፣ ለረድኤት ግልጋሎት በሮችን በማንኳኳትና የድንጋጌ አፈጻጻምን በመቆጣጠር" ረገድ በስምንት አካባቢዎች እገዛ ማድረግ ጀምረዋል። የጦር ሠራዊት አባላቱ የታጠቁ አይደሉም።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ነዋሪዎች ከትባት እንዲከተቡ እያበረታቱ ነው። የክትባት መስጫ ክሊኒኮችን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት 13 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኗን አስታወቀች። በቫይረሱ ከተጠቁት ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። ሁሉም በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶባቸው ያሉ አካባቢዎች ነዋሪዎች ናቸው። በጠቅላላው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል።
በጅሮንድ ካሜሮን ዲክ በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች እገዛ እንደሚያገኙ አስታውቀዋል
ተጥሎ ያለው ገደብ በ Brisbane, the Gold Coast, Ipswich, Lockyer Valley, Logan, Moreton Bay, Noosa, Redland, Scenic Rim, Somerset and the Sunshine Coast እስከ እሑድ ኦገስት 8 ተራዝሟል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ቪክቶሪያ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
- ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታ ሆኖ ሲቀጥል፤ የተወሰኑ ተመልካቾችን ያካተቱ የስፖርት ውድድሮች እንዲካሄዱ ተፈቅዷል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤