- ቪክቶሪያ ውስጥ በቅርቡ በቫይረስ ከተያዙት 45 ፐርሰንቱ ዕድሜያቸው ከ30 በታች ነው
- ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌልስ ሊዝሞር ላይ የተጣለው የሰባት ቀናት ገደብ ዛሬ ይጀምራል
- ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ የካንብራ ነዋሪዎች ውስጥ ከ93 ፐርሰንት በላይ ተከትበዋል
- ኩዊንስላንድ አንድ ነዋሪዋ በቫይረስ መያዙን አስመዘገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,377 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአራት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
የሚልዱራ ቁሻሻ ፍሰት ውስጥ ቫይረስ ተከስቶ ተገኝቷል። የሪጂናል ቪክቶሪያን ሞርዌል እና ሼፐርተንን አክሎ ተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ተመዘገቡ
የሜልበርን ነዋሪዎች በስድስት ገደቦች ውስጥ 246 ቀናትን በማሳለፍ የአርጀንቲናን መዲና ቦይኖስ አይረስን የገደብ ሬኮርድ አልፈዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 623 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ሊዝሞር ላይ እስከ ኦክቶበር 11 ፀንቶ የሚቆይ ገደብ ተጣለ። ከሴፕቴምበር 28 ጀምሮ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችንም ይጨምራል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደቦቿን ለማርገብ የመጨረሻው ሳምንት ላይ በምትገኝበት ወቅት ኦክቶበር 2 ዕኩለ ለሊት ላይ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 67.1 ደርሷል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ ሁለት ነዋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት 16 የኮቪድ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አምስቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል አንድ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
የክትባት መመዘኛን ከሚያሟሉ ነዋሪዎች ውስጥ 93 ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የኩዊንስላንድ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ቁጥር ጨምሯል አንድ ግለሰብ በቫይረስ ተጠቅቶ ለ10 ቀናት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲዘዋወር ነበር
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤