ኒውሳውዝ ዌልስ በፌርፊልድ ፤ ካንተርበሪ - ብላክታወን አና ሊቨርፑል የሚኖሩ ነዋሪዎች በስራ ሳቢያ ከአካባቢያቸው እንዲወጡ የሚያስችላቸውን የተፈቀዱ የስራ መስክ ዝርዝሮችን ጨመረች ።
በቪክቶሪያ በኮቪድ-19 የተጋላጡ አካባቢዎች ቁጥር መጨመሩ ቀጠለ ።
ኒውሳውዝ ዌልስ 105 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦችን ቁጥር ያስቆጠረች ሲሆን ፤ ከነዚህ ውስጥ 66 የሚሆኑት ቀድሞ ከታወቀ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ናቸው ፤ በአንጻሩ የቀሩት 33 ተያዦች ምንጭ እስከ አሁንም ደረስ ያልታወቀ እና በምርመራ ላይ የሚገኝ ነው ። በተያያዘም እድሜያቸው በ90ዎቹ ውስጥ ያሉ አንዲት ሴት የደቡብ - ምስራቅ ሲድኒ ነዋሪ ህይወታቸው አልፏል ።
በፌርፊልድ ፤ ካንተርብሪ - ብላክታወን አና ሊቨርፑል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው መውጣት የተከለከሉ ሲሆን ፤ ነገር ግን በጤና ክብካቤ ፤ በድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የገበያ ማእከላት ፤ በመጠጥ መሸቻ ሱቆች ፤ አንስተኛ ሱቆች ፤ የጋዜጣ መሸጫዎች ፤ ቢሮዎች፤ የቤት እንሣት አገልግሎት መስጫዎች እና የአትክልት ስፍራ የሚሰሩ ባላሙያዎች መውጣት ተፈቅዶላቸዋል ።
ከሰኞ ጁላይ 19 ከጠዋቱ 12.01 ጀምሮ የግንባታ ስራዎች ፤ አስቸኳይ ያልሆኑ የጥገና ስራዎች ፤ የጽዳት አገልግሎት እና የቤት ውስጥ ጥገና ስራ የሚቋረጥ ይሆናል ። ይህ ገደብ በኒውሳውዝ ዊልስ እስከ 500,000 የሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞችን ስራ እንደሚያስተጓጉል ከውዲሁ ተገምቷል ።
በአካባቢዎት ስርጭቱ ያላበትን ቦታ ለማወቅ ዝርዝሮቹን ወይም ካርታውን ይመልከቱ፦ በአሁን ሰአት የተቀመጠው ገደብ እስከ አርብ ጁላይ 30 እንደሚቆይ ይጠበቃል ።
ቪክቶርያ
ቪክቶርያ 16 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦችን ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን ከነዚህም መካከል ሁለቱ ከውጭ አገር በመጡ ሰዎች ሳቢያ የመጡ ናቸው ። በአሁን ሰአትበቪክቶሪያ ያለው የቫይረስ ተያዦች ቁጥር 70 ደርሷል።
215 የሚሆኑ አካባቢዎች ለቫይረሱ የተጋላጡ መሆናቸው ታውቋል ። በቅርብ ከታወቁት አካባቢዎች መካከለም አልቶና ሜዶውስ ፤ ኪው ፤ እና ትሩጋኒና ይገኙበታል።
የደቡብ ምስራቅ ፊሊፕ አይላንድ አካባቢ ነዋሪዎችም ምርምራ እንዲያደርጉ ግፊት ተደርጎባቸዋል ። በአካባቢዎት ስርጭቱ ያላበትን ቦታ ለማወቅ ዝርዝሮቹን ውይም ካርታውን ይመልከቱ ይመልከቱ፦ ለአምስተኛ ጊዜ የተጣላውም ገደብ በመጪው ማክሰኞ ጁላይ 20 ከምሽቱ 11፡59 ላይ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ።
ባለፉት 24 ሰአታት በመላው አውስትራሊያ
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ እና ኩዊንስላድ በማህበረሰቡ ውስጥ ምንም የተላለፈ ቫይረስ የለም
- በደቡ አውስስትራሊያ ወደ 100,000 የሚደርስ ክትባት አደላይድ ሾው ግራውንድ በዌይቪል ደርሷል ።
- ታዝማንያ ድንበሯን ለሁሉም የኒውሳውዝ ዌል ነዋሪዎች ዝግ አድርጋለች
የኢድ አላድሀ በአል ( የመስእዋትነት በአል) ሰኞ ጁላይ 19 የሚጀምር ሲሆን በበአሉ የጸሎት ስነ ስራት ወቅትም ራስን እና ሊሎችን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን መውሰድ ይገባል ፦
- ጸሎትን ከቤት ማድረግን ይምረጡ
- በርካታ ሰዎች ከሚገኙበት ስፍራ ከመሄድ ይታቀቡ
- የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ያድርጉ
- የርስዎን የመስገጃ ምንጣፍ ይጠቀሙ
የኮቪድ-19 አፈታርኮች
ጤነኛ ወጣቶች በኮቪድ-19 አይያዙም ፡ የሚገድለውም አዘውንቶችን እና የጤና ቸግር ያለባቸውን ብቻ ነው ።
የኮቪድ-19 እውነታ
የእድሜ ባለጸጋዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል እንዲሁም ተያያዝ የጤና ችግር ያለባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል ፤ ነገር ግን ጤነኛ ወጣቶችንም ይጎዳል እንዲሁም ይገድላል ።
ለይቶ ማቆያ ፤ ጉዞ፣ የመመርመሪያ ክሊኒኮች ፤ እና የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያ
የለይቶ ማቆያ እና የመመርመሪያ ክሊኒኮች የሚመሩት እና ተግባራቸውን የሚከውኑት በክልሎቹ እና ግዛቶቹ መንግስታት ነው ፦
ከአውስትራሊያ ውጪ እንዴት ማጓዝ እንደሚችሉ ተጨማሪ ማረጃን ማግኘት ይችላሉ ። ኣለማቀፍ በረራዎችን በተመለከተ ጊዜያዊ የሆኑ እርምጃዎች በየጊዜው በመንገስት የሚከለሱ እና የሚሻሻሉ ናቸው ስለሆነም ድረገጽን ይመለከቱ ።
በሚኖሩበት ክልል እና ግዛት ያለውን ጠቃሚ መረጃ ከ , , , , , , . ያግኙ
የኒውሳውዝዊልስ የመድብለ ባህል ጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት ትርጉም መረጃዎችን በተመለከተ ፦
የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የመመርመሪያ ክሊኒኮችን በተመለከተ ፦
የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያን መረጃ በተመለከተ፦