የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በሙከራ ፕሮግራም ልታስገባ ነው

*** ቪክቶሪያ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 59 ላሉ ከትባት ልትሰጥ ነው

COVID-19 update

Victorian Police officers patrol through Bourke Street Mall ahead of a planned rally in Melbourne, Friday, September 24, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ አንድ ሶስተኛ ልጆች የመጀመሪያ ክትባታቸውን ተከትበዋል
  • ቪክቶሪያ የሞደርና ክትባት ስርጭት መጨመሩን አስታወቀች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ቁጥር እየናረ ነው
  • የክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ ሃምሳ ፐርሰንት አውስትራሊያውያን ሙሉ ክትባት ተከትበዋል

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,043 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ፋይዘር፣ ሞደርና እና አስትራዜኔካ ሙሉ ክትባቶችን የተከተቡ 500 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በሙከራ ፕሮግራም ልታስገባ ነው። 

የኮቪድ-19 ቫይረስ ናሙናዎች በምዕራባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ Lightning Ridge በደቡባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ Jindabyne በደቡባዊ ቴብላንድስ Crookwell እና በሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ South Lismore ተገኝተዋል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ 

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 733 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 84 ፐርሰንቱ ዕድሜያቸው ከ50 በታች የሆኑ ናቸው። የአንድ ሰው ሕይወም አልፏል።

የጤና ሚንስትር ማርቲን ፎሊ በመላው ቪክቶሪያ ከ700 በላይ መድኃኒት ቤቶች በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ከ 300,000 በላይ የሞደርና ክትባቶች እንደሚደርሷቸው አስታወቁ። እንዲሁም፤ ከ 32,000 በላይ ተጨማሪ ሞደርና ክትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 59 ላሉ መከተቢያነት ለተንቀሳቃሽ የክትባት ጣቢያዎች ይሰጣሉ።  

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 19 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች።

አንዲት በሰሜን ካንብራ ያለ የካልቫሪ ሄይደን የተጠዋሪ ማኅበረሰብ ነርስ በኮቪድ-19 ተይዛለች። የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የተጋላጭነት ሥፍራዎች 450 ደርሰዋል 

የኮቪድ-19  ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to                                                                                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የታዝማኒያ የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ ዛሬ ጀምሯል። መንገደኞች በድንጋጌው መሠረት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ማረጋጋጫ ማቅረብና ከአውሮፕላን ማረፊያ የግል እንጂ የሕዝብ ትራንስፖርት ግልጋሎትችን አለመጠቀም ይጠበቅባቸዋል። 

Share
Published 24 September 2021 2:25pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends