የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ የጣለችውን የሰዓት ዕላፊ ገደብ አነሳች

*** ቪክቶሪያ ውስጥ ባላራት ላይ ገደብ ተጣለ

COVID-19 update

Members of the public wear face masks as they go about their daily lives in Marrickville, Sydney, Wednesday, September 15, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ16 በላይ የሆኑ 47.5 ፐርሰንት ነዋሪዎች ሙሉ ክትብስት ተከትበዋል
  • ዛሬ ዕኩለ ለሊት ላይ ሺፐርተን ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ያበቃል
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከታቢዎች ቁጥር 75 ፐርሰንት ሊደርስ ተቃርቧል
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ አንድም ሰው አልተመዘገበም

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,1259 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን 80 ፐርሰንት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ መሆኑን አስታወቁ፤ የምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎች እንዳይዘናጉ አሳሰቡ።

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ይነሳል። በኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት ፍኖተ ካርታ መሠረት ሁለት ዙር የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት ሲደርስ ተጥለው ያሉ ገደቦች ይላላሉ። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 423 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ባላራት ላይ ከዛሬ እኩለ ለሊት ጀምሮ ገደብ ተጥሏል። ነዋሪዎች ከሰዓት ዕላፊ በስተቀር ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናት ሜልበር ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ይመለከታቸዋል። ሺፐርተን ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከቫይረስ ነፃ በመሆኗ ተጥሎባት የነበረው ገደብ ዛሬ እኩለ ለሊት ላይ ይረግባል። 

ተጨማሪ የባቡር ጣቢያ ሠራተኛ በቫይረስ በመያዙ አብዛኛዎቹ የቪክቶሪያ ሪጂናል ባቡሮች ገልጋሎት ከመስጠት እንዲገቱ ተደርጓል። አውቶቡሶች የ V/Line ግልጋሎቶችን ተክተው ለተሳፋሪዎች የትራንስፖርት ግልጋሎቶችን ይሰጣሉ። 

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

13 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።  

ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት 75 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ ዋና ሚኒስትር አንድሩ ባር ገለጡ።

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ .                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • በኖርዘን ቴሪቶሪ ደረጃ ሶስት ኮቪድ ፕላን መሠረት ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሠራተኞች ከትባት እንዲከተቡ ግድ ይሰኛሉ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 15 September 2021 2:27pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends