የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪምየር በዲሴምበር 1 "መደበኛ ህይወት" እንደሚጀመር ተስፋቸውን ገለጹ

ይህ በአውስትራሊያ ሴፕቴምበር 27 የተሻሻለ የኮሮናቫይረስ መረጃ ነው

Birrong Leisure and Aquatic Centre

Public arrives at the Birrong Leisure and Aquatic Centre, after outdoor swimming pool were allowed to open today in Sydney, Monday, September 27, 2021. Source: AAP Image/Bianca De March

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከተጣለው ገደብ ለመውጣት ሶስት ደረጃ ያለውን ፕላን አወጣች
  • ቪክቶሪያ የክትባቱን ሂደት ለማፋጠን ለቤተሰብ ሀኪሞች እና መድሃኒት ቤቶች ተጨማሪ የገንዘብ ድጎም አደረገች
  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ሰው ህይወቱን አጣ


ኒው ሳውዝ ዌይልስ  

በኒው ሳውዝ ዌይልስ 787 የሚሆኑ ነዋሪዎች በማህበረሰብ ውስጥ በተዛማተ ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 12 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክሊያን እንዳረጋገጡትም በአሁን ሰአት ያለው ገደብ ከኦክቶበር 10 በኋላ እንደሚላላ ሲሆን 70% በሚሆነው ፕላኑ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ፡፡ ይሁንና ወደ ሌሎች ከተሞች መንቀሳቀሰን በተመለከተ የተጣለው ገደብ ለጊዜው የሚቆይ ሲሆን ፤ የተከታቢዎቹ ቁጥር 80% እስካልደረሰ ድረስ ባለበት የሚቀጥል ይሆናል ፡፡

ፕሪምየሯ አያይዘው እንደገጹት ገደቦችን ለማላላት የተቀመተው ፕላን በሚያሳየው መሰረት ሁለቱንም ክትባቶች የውሰዱት ሰዎች ቁጥር 80 % ከደረሰም ፤ በሰርግ እና ቀብር ታዳሚዎች ቁጥር ላይ የተቀመጠው ገደብ ፤ እንዲሁም በማህበረሰብ ስፖርቶች ላይ የተጣለው ገደብ ይነሳል ፤ በመኖሪያ ቤቶችም እስከ 10 የሚሆኑ ሰዎች መገኘት ይችላሉ ፡፡

Click to  today. 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 705 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ፤ አንድ ሰው ህይወቱን አጥቷል ፡፡

  •  ፕሪምየር ዳናኤል አንድሪው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሆኖ የተከታቢዎቹ ቁጥር አነስተኛ በሆኑባቸው አካባቢዎች  የክትባቱን ሂደት ለማፋጠን ለቤተሰብ ሀኪሞች እና መድሃኒት ቤቶች ተጨማሪ የገንዘብ ድጎም እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል ፡፡ በዚህም መሰረት ሞርላንድ ፤ ብሪምባንክ ፤ ካርዲኒያ ፤ ኬሲ ፤ ዳረብን፤ ግሬተር ዳንዲኖንግ ፤ ሆብሰን ቤይ ፤ ሜልተን ፤ ዊተልሲ ፤ ዊንድሰር እና ሂውም የገንዘብ ድጎማው ተጠቃሚዎች ናቸው ፡፡
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የኮቪድ-19  ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to                                                                                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • የፌዴራል ቱሪዝም ሚኒስትር ዳን ቲሃን መንግሥት የክትባት ፓስፖርትን አካትቶ አስገዳጅ የሆቴል ወሸባ አልባ ዓለም አቀፍ ጉዞን "ቢያንስ ለገና" አምቺ አሠራሮችን ግብር ላይ ለማዋል እየተሰናዳ መሆኑን ገለጡ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ACT  and 
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

 
 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 27 September 2021 4:06pm
Updated 27 September 2021 4:12pm
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends