የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ቁጥሩ ሊያሻቅብ የሚችለውን የኮሮናቫይረስ ሕሙማን የክፍለ አገሩ ሆስፒታሎች ሊቋቋሙት እንደሚችሉ ገለጡ

*** የቤቶች ሚኒስትር ሪችድ ዌይን ተከራይ ሆነው ከ30 ፐርሰንት በላይ ገቢ ላጡና አከራይ ሆነው 20 ፐርሰንት ወይም ከዚያ በላይ የገቢ እጦት ለደረሰባቸው የድጎማ ክፍያ የሚቸር አዲስ ፕሮግራም መጀመሩን አስታወቁ

COVID-19 update

NSW Ambulances park in the receiving bay for the Emergency Department at the Blacktown Hospital in Sydney. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 40.8 ፐርሰንት የክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ ነዋሪዎች የሁለተኛ ዙር ክትባት ተከትበዋል
  • ቪክቶሪያ በኪራይ ቤት ሳቢያ ለታወኩ ሰዎች አዲስ ፕሮግራም አወጣች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የአስትራዜኔካ ሁለተኛ ዙር ክትባት የቆይታ ጊዜን ከአራት እስከ ስምንት ሳምንታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንዲሆን ወሰነች
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ በፋይዘር ክትባት ክተባ ላይ የተሳታፊ ጠቅላላ ሐኪሞች ቁጥር እየጨመረ ነው

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,281 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 831ዱ ከሲድኒ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ናቸው። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

እንደራሴ በርጂክሊያን ኒው ሳውዝ ዌይልስ 70 ፐርሰንት የክትባት መጠን ላይ ከደረሰ በኋላ ለሆስፒታል የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር የዳታ ማሳያ እንደሚያመለክት ገለጡ። በአሁኑ ወቅት 177 የኮቪድ ሕሙማን በፅኑዕ ሕመምተኞች ክፍል ሲገኙ 67 በአየር መተንፈሻ አጋዥ ቁሶች የሚረዱ ናቸው።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ   

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 246 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 121ዱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። 

የቤቶች ሚኒስትር ሪችድ ዌይን ተከራይ ሆነው ከ30 ፐርሰንት በላይ ገቢ ላጡና አከራይ ሆነው 20 ፐርሰንት ወይም ከዚያ በላይ የገቢ እጦት ለደረሰባቸው የድጎማ ክፍያ የሚቸር አዲስ ፕሮግራም  መጀመሩን አስታወቁ

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 11 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል፤ ሰባቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ነው። 

የካንብራ ነዋሪዎች   በመጠቀም አለያም በስልክ ቁጥር (02) 5124 7700 ከማለዳው 7.00am እስከ ምሽቱ 7.00pm በመደወል የአትራዜኔካ ሁለተኛ ዙር ክትባት ቀነ ቀጠሯቸውን ማስያዝ ይችላሉ። 

ለክትባትዎን ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ  የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት እየሰጡ ሲሆን በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ 642 ጠቅላላ ሐኪሞች ይታከላሉ  
  • ከእንግሊዝ ጋር በተካሔደው የክትባት ልውውጥ ስምምነት መሠረት 500,000 ያህል የፋይዘር ክትባት በዛሬው ዕለት ሴፕቴምበር 6 ሲድኒ ገብቷል
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 


Share
Published 6 September 2021 3:09pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends