የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ 70 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ላይ ደረሰች፤ የአካል እንቅስቃሴ ገደቦችን ከላች

*** ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 176 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ መጠቃታቸውን አስታወቀች፤ 128ቱ ከሰሜናዊና ምዕራባዊ ሜልበርን አካባቢዎች ናቸው።

COVID-19 update

Members of the public exercising at Tempe in Sydney, Monday, August 23, 2021. Source: AAP

  • በደቡባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ አዲስ የኮቪድ ቆሻሻ ፍሳሽ ምርመራዎች
  • ቪክቶሪያ በዚህ ዓመት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ዕለታዊ ቁጥር አስመዘገበች
  • 68 ፐርሰንት የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች ተከተቡ
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ሌላ አንድ የከባድ ጭነት መኪና ሾፌር በቫይረስ ተጠቃ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,288 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዛሬ ማምሻ ላይ 70 ፐርሰንት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባታቸውን ተከትበው ያጠናቅቃሉ 

ከዓርብ ሴፕቴምበር 3 ጀምሮ ለ12 የአካባቢ መንግሥት የስጋት ቀዬዎች ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው የአንድ ሰዓት የአካል እንቅስቃሴ ገደብ ይነሳል  ሌሎች ገደቦች ፀንተው ይቆያሉ።

በቤጋ፣ ኩማና በቡማደሪ ኢላዋራ ሾልሄቨን ኮቪድ-19 ፍሳሽ ቆሻሻ ውስጥ ተከስቷል። በአካባቢው በቫይረስ መጠቃታቸው የተመዘገቡ ሰዎች ባለመኖራቸው ስጋትን ጭሯል።  

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ   

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 176 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 128ቱ ከሰሜናዊና ምዕራባዊ ሜልበርን አካባቢዎች ናቸው። 

ከ11.59 pm ጀምሮ የመጫወቻ ሥፍራዎች ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ከአንድ ወላጅ ወይም ተከባካቢ ጋር ክፍት ይሆናል። የመጫወቻ ሥፍራዎቹ  QR ኮዶች የሚኖራቸው ሲሆን አዋቂዎች ለመብል ወይም ለመጠጥ በሚል ሳቢያ የፊት ጭምብላቸውን ማውለቅ አይችሉም።  

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 12 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ ስምንቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

ከሴፕቴምበር 3 አንስቶም ትራንስፖርት ካንብራ ማናቸውም ለክትባት ወደ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ኮቪድ-19 ክሊኒክ ለሚሄዱ ሁሉ ነጻ የአውቶቡስና ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ያቀርባል። 

የክትባት ቀጠሮዎን እንደምን ማስያዝ እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን ይጫኑ   

ያልፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ሁለት አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ግንኙነት የሌላቸው የከባድ ጭነት መኪና ሾፌሮች በቫይረስ መጠቃታቸውን አስታወቀች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 2 September 2021 2:16pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends