- በመላው አውስትራሊያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሆስፒታል የተዳረጉ ሕሙማን ቁጥር እየናረ ነው። ትናንት እሑድ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 1,066 ደርሶ የነበረው የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር ዛሬ 1,204 ደርሷል
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የኮቪድ-19 የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ታካሚዎች ከ83 ወደ 95 ከፍ ብሏል። ቪክቶሪያ ውስጥ 491 በኮሮናቫይረ የተጠቁ ሕሙማን ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ሲሆን በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል የአየር መተንፈሻ ተገጥሞላቸዋል
- የጤና አገልግሎቶች ሠራተኛ ማኅበር የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሆስፒታል የጤና ሠራተኞች በሥራ ብዛት ሊሰላቹና የጤና ሥርዓቱም ከሁለት እስከ ሶስት ባሉ ወራት በብርቱ ፈታኝ ሁነት ላይ ሊደርስ እንደሚችል አሳሰበ
- በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የፌዴራል መንግሥቱ 84 ሚሊየን ፈጣን መመርመሪያዎችን (RATs) ለግዢ እንዳዘዘና ከፍለ አገራትም ተጨማሪ አቅርቦቶችን እንደሚያገኙ ገለጡ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ፈጣን መመርመሪያዎች በቅርብ ንኪኪ ለተፈረጁ ሰዎች በነፃ ሊሰጥ እንደሚችልና ሆኖም ለሁሉም ሰው በነፃ እንደማይሰጥ አስታወቁ
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 20,794 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ቪክቶሪያ ውስጥ 8,577 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኩዊንስላንድ 4,249 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ አንድ ሰው ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርጓል።
ታዝማኒያ 466 ሰዎች ተጠቅቶባታል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 514 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤