የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ የመጀመሪያው የኦሚክሮን ኮቪድ-19 ተጠቂ ሞት ተመዘገበ

*** የክፍለ አገር መንግሥታት አውስትራሊያውያን አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር በጤና ክብካቤ ሥርዓቱ ላይ ጫና ላለማሳደር ወደ ኮቪድ-19 መመርመሪያ ጣቢያዎችና የድንገተኛ ዲፓርትመንቶች ከመሔድ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ

COVID-19 update

Queues for Covid-19 tests at Bondi Beach, Sydney. Source: AAP

  • ኔው ሳውዝ ዌይልስ በመጀመሪያነቱ የታወቀውን የኦሚክሮን ኮቪድ-19 ሞት አስመዘገበች

  • የክፍለ አገር መንግሥታት አውስትራሊያውያን አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር በጤና ክብካቤ ሥርዓቱ ላይ ጫና ላለማሳደር ወደ ኮቪድ-19 መመርመሪያ ጣቢያዎችና የድንገተኛ ዲፓርትመንቶች ከመሔድ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩባቸውና ምርመራ እንዲያደርጉ መመሪያ የተሰጣቸው ብቻ የPCR ምርመራ እንዲያደርጉ እያበረታታ ነው

  • የቪክቶሪያ መንግሥት አሁን ያለው የምርመራ አሠራሩ ላይ ለውጦችን በማድረግ በቫይረስ ከተጠቃ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ ያላቸው ሰዎች ፈጣን ምርመራን በመጠቀም ራሳቸውን ከወሸባ እንዲያገሉ ለማድረግ ወጥኗል

  • ከዛሬ ጀምሮ  QR check-ins ከቡና ቤቶች፣ ምግብ ቤቶችና ክለቦች የርቀት መጠን ጋር ተያይዞ ግዴታ ሆኖ ተመልሷል

  • የደቡብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ስቴቨን ማርሻል የመስተንግዶ ግልጋሎቶችና የቤት ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር መጠን ጨምሮ ተጨማሪ የኮቪድ-19 ገደቦችን ጣሉ

  • ደቡብ አውስትራሊያ ወደ ግዛቷ ለመዝለቅ ግዴታ የነበረውን የPCR ምርመራ ድንጋጌ አነሳች

  • አራት የእንግሊዝ ተጫዋጮች በቫይረስ በመጠቃታቸው የዓለም አቀፍ ክሪኬት ግጥሚያ እክል ገጥሞታል

  • ዩናይትድ ኪንግደም እንደ ዌልስ፣ ስኮትላንድና ሰሜናዊ አየርላንድ ሁሉ የኮቪድ-19 መናርን ለመግታት አዲስ ገደቦችን ስትጥል እንግሊዝ አጭር የእንቅስቃሴ ገደቦችን ለመጣል እያሰበች ነው

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 6,324 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የሶስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,999 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 784፣ ደቡብ አውስትራሊያ 774 እንዲሁም የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 189 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተውባቸዋል። 

ታዝማኒያ 35 ሰዎች በቫይረስ ተይዘውባታል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ .

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አራት ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።  

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


 


Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends