- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ፈቃድ ላላቸው ሠራተኞች አዲስ የክትባት መስፈርቶች ወጡ
- ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ሊራዘም ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 13 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ
- ኩዊንስላንድ አንድ የቤት ውስጥ ወሸባ ገብቶ ያለ ግለሰብ በቫይረስ መያዙን አስታወቀች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,218 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 887ቱ ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በጠቅላላው ከኮቪድ ጋር በተያያዘ 145 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
ከሰኞ ሴፕቴምበር 6 ጀምሮ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች ከቀዬአቸው ዉጪ ተጉዘው ለመሥራት ቢያንስ የአንድ ዙር ክትባት የመከተብ ግዴታ ይኖርባቸዋል
የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች፣ ዕድሜያቸው ከ16- 19 ሆኖ ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ለሆኑና ነዋሪነታቸው ወይም የሥራ ገበታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሆኖ በሕፃናት ክብካቤ፣ የግብረ አካል ጉዳተኞችና የምግብ ሠራተኞች ዘርፍ ለሆኑ የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል , and .
የኮቪድ-19 ከትባት ማረጋጋጫ እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 92 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 30ዎቹ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም።
በጠቅላላው በቫይረሱ ከተያዙት 778 ሰዎች ውስጥ 500 ያህሉ የሰሜንና ምዕራብ ነዋሪዎች መሆናቸውን እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ጠቁመው በታካይነትም ቀነ ገደቡ ሴፕቴምበር 2 የሚያበቃውን ገደብ ለማርገብ አዋኪ መሆኑን አስታውቀዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ከሴፕቴምበር 8 ጀምሮ ቡንዳል በሚገኘው የብሪስበን የመዝናኛ ማዕከል የመጠነ ሰፊ የክትባት ማዕከል ትከፍታለች
- የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የ በ TGA የጸደቀውን ክትባት ለሚከተቡ አውስትራሊያውያን ጥበቃ እንደሚቸራቸው ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤