- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዳግም አሻቀበ
- ቪክቶሪያ ውስጥ አብዛኛዎቹ በኮቪድ-19 የተጠቁት ወጣቶች ናቸው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮቪድ-19 ግብረ ኃይሏን አጠናከረች
- ኩዊንስላንድ የሆቴል ወሸባ ፕሮግራሟን ገታች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 919 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች፤ 37 በማኅበረሰብ ውስጥ የተዛመቱ ናቸው። የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
Guildford, Auburn, Merrylands, Greystanes, Granville, Punchbowl, Yagoona እና Blacktown ስጋት ካለባቸው ክፍለ ከተማነት አልወጡም።
ዋና የጤና መኮንን ኬሪ ቻንት የፅኑዕ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ ከሚገኙ 113 ህመምተኞች ውስጥ 98ቱ ያልተከተቡ መሆናቸውን ገልጠዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 45 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 28ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ እንዳስታወቁት ከ538 በቨይረስ የተጠቁ ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በለይ የሆኑቱ ከ30ዎቹ በታች ያሉ ሲሆኑ 114 ዕድሜያቸው ከዘጠኝ ዓመት በታች ነው።
ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 17 የፋይዘር ክትባት መከተብ የሚችሉ ሲሆን ከ18-39 የሚገኙ ከአስትራዜኔካ ወይም ፋይዘር ከትባቶች አንዱን መርጠው መከተብ ይችላሉ። ዕድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ ለሆኑት ግና አማራጩ ክትባት አስትራዜኔካ ብቻ ነው።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 9 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 176 ደርሷል።
የጤና ሚኒስትር ራቼል ስቴፈን ነርሶች፣ ተማሪ ነርሶችና ተማሪ አዋላጆች ከታሳቢ የክትባት አቅርቦት ጭማሪ ጋር የክትባት ሂደቱም አብሮ እንዲሄድ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጠዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- በሆቴል ወሸባ መጨናነቅ ሳቢያ ኩዊንስላንድ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ እና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ላይ እስከ ሴፕቴምበር 8 ድረስ እገዳ ጥላለች
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤