- ቪክቶሪያ ለከቤት ውጪ ንግድ የምጣቤ ሃብት መደጎሚያ እንደምትሰጥ አስታወቀች
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ
- ታዝማኒያ በነደፈችው ዕቅድ መሠረት ገደቦቿን ልታነሳ ነው
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,903 በቫይረስ ተጠቁ፤ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
የሥራ ሚኒስትር ጃላ ፑልፎርድ የአካል እንቅስቃሴ ማጠንከሪያ፣ ችርቻሮ፣ የውበት ሳሎንን ለመሳሰሉ ንግዶችና ድርጅቶች የከቤት ውጪ ንግድ መቋቋሚያ የሚሆን $54 ሚሊየን ዶላርስ የቪክቶሪያ መንግሥት መመደቡን አስታወቁ
ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከ89.2 ፐርሰንት በላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 66.5 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ሐሙስ ኦክቶበር 21 ዕኩለ ለሊት ላይ ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ይረግባሉ። ዓርብ ኦክቶበር 22 ሁሉም ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 265 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ዘጠና ፐርሰንት ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 80.3 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
በዛሬው ዕለትየ12ኛ ክፍል 1ኛ ክፍልና የሙዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ከሌሎች ቀደም ብለው ተመለስዋል። የተቀሩት ተማሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 17 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 11ዱ የቫይረሱ መስፋፋት ከታወቀባቸው ሥፍራዎች ናቸው።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ አንድም በቫይረስ የተያዘ ግለሰብ አላስመዘገበችም።
- ደቡብ ታዝማኒያና መዲናይቱ ሆባርት በተነደፈላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ዛሬ ምሽት 6pm ላይ የተጣሉባቸው የኮሮናቫይረስ ገደቦች ይነሱላቸዋል።