የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ የሆቴልና የቤት ውስጥ ወሸባን ከላች

*** ቪክቶሪያ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ ጥላ የነበረችውን የወሰን ገደብ አነሳች

COVID-19 update

Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ተከትበው ወደ ግዛቷ ለሚዘልቁ የወሸባ ግዴታን አነሳች
  • ቪክቶሪያ ሙሉ ክትባት ተከትበው ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሚመጡ የወሸባ መሥፈርቷን ገታች
  • እስከ ኖቬምበር 1 ድረስ ወደ ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ መሔድ አይቻልም

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 399 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

እንደራሴ ዶሜኒክ ፔሮቴይ ከሰኞ በኋላ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ የተወሰኑ ገደቦች እንደሚረግቡ አስታወቁ። 

ከኖቬምበር 1 ጀምሮም ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የሆቴልና የቤት ውስጥ ወሸባ እንደማይኖር አስታውቀዋል። መንገደኞች ከመሳፈራቸው በፊትና እዚህም እንደደረሱ ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ምርመራዎች እንደሚካሄዱም ገልጠዋል። መንገደኞች የተከተቧቸው ክትባቶች ዓይነት በአውስትራሊያ ፈዋሽና ቁስ አስተዳደር ዕውቅና የተቸራቸው መሆን ይገባዋል። ወደ አገር ተመላሽ አውስትራሊያውያን ቅድሚያ ያገኛሉ። 

ከሰኞ ጀምሮ በቤት ውስጥ የሰዎች መሰባሰብ ቁጥር ወደ 20 ከፍ ሲል በውጭ እስከ 50 ከፍ ብሏል።  

እስከ ኖቬምበር 1 ድረስ ወደ ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ መጓዝ አይቻልም። 

 Find a  near you.

ቪክቶሪያ
ከሚቀጥለው ማክሰኞ ጀምሮ ቪክቶሪያ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ የኒው ሳውዝ ነዋሪዎች የወሸባ መስፈርቶቿን ታነሳለች።

በዛሬው ዕለት 2,179 የቪክቶሪያ ነዋሪዎች በኮቪድ-19 ጠጠቅተዋል፤ ስድስት ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ተጓዦች ቪክቶሪያ ሲደርሱ ከቫይረስ ላልፉት 72 ሰዓታት ነፃ መሆናቸውን የምርመራ ማረጋጋጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። 

 የኮቪድ-19 ክትባት ግዴታ የተጣለባቸው የሥራ መስክ ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ ለመሰማራት የመጀመሪያ ክትባት የመከተብ ድንጋጌ ግብር ላይ ውሏል።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 35 ሰዎች በቫይረስ ተጠተዋል። በድምሩ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 1,394 ደርሷል። አንዲት የ70 ዓመት አረጋዊት የአረጋውያን መጠወሪያ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል።      

ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ከኖቬምበር 1 ጀምሮ 97 ፐርደንት ትክክለኛ የምርመራ ውጤት የሚያሳይ የኮቪድ-19 ራስን በራስ መመርመሪያ በየመድኃኒት ቤት መደርደሪያዎች ላይ ለሸማቾች ይቀርባል። 
  • የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና አውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ በወርኃሴፕቴምበር 138,000 ሰራተኞች ሥራዎቻቸውን እንዳጡ ገለጠ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 


Share
Published 15 October 2021 5:06pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends