የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ትምህርት ቤቶቻቸው ተመለሱ

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 1,461 በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል፤ አንዲት በ20ዎቹ ዓመት ውስጥ ያለች ሴትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

COVID-19 update

Students of Hunter School of the Performing Arts celebrate their return on campus in Newcastle after months of lockdown. Source: Supplied by Hunter School of the Performing Arts

  • የማጠናከሪያ ክትባት ከሁለተኛ ዙር ክትባት ስድስተኛ ወር በኋላ ሊሰጥ ነው
  • ቪክቶሪያ የነባር ዜጎች የክትባት መጠንን ከፍ ለማድረግ ጥረቶቿን አደሰች
  • ሁሉም የኒው ሳውዝ ዌይልስ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ትምህርት ክፍሎቻቸው ተመለሱ

 ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,461 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ አንዲት በ20ዎቹ ዓመት ውስጥ ያለች ሴትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ በነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ዘንድ የክትባት ግንዛቤ ማስጨበጫን ከፍ ለማድረግ ጥረቶች መጨመራቸውን አስታወቁ። በዚህም መሠረት 'ዝቅተኛ ደረጃ' ክትባት ባለባቸው አካባቢዎች ቀጣይነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች ግብር ላይ እንደሚውሉ ገልጠዋል። 

ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ያሉ የአቦርጂናል ማኅበረሰብ አባላት 80 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን በጠቅላላው ቪክቶሪያ ውስጥ በተመሳሳይ የዕድሜ ፈርጅ ያሉ 90 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል።

ከዓርብ ኦክቶበር 29 ጀምሮ ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ መጓዝና ከቤት ውጪ የፊት ጭምብል አለማጥለቅን አካቶ ተጨማሪ ገደቦች ይነሳሉ። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 294 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ሁሉም የኒው ሳውዝ ዌይልስ ተማሪዎች ዛሬ ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ተመልሰዋል። ይሁንና ከሙሉ ክትባት ግዴታ ጋር ተያይዞ ሁሉም አስተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች አይመለሱም። 

“ከ95 ፐርሰንት በላይ መምህራኖቻችን ተከትበዋል። ያም ትምህርት ቤቶቻችን ጥንቃቄን በተላበሰ ሁኔታ ለመክፈት አስችሎናል። እጅጉን የላቀ ጥረት ነው" በማለት እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ ተናግረዋል። 

ሲድኒ ውስጥ ባለፈው ኦገስት በሕዝብና የግል ሆስፒታሎች ታግዶ የነበረው አስቸኳይ ያልሆኑ ቀዶ ሕክምና መሰጠት ተጀምሯል።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

ኩዊንስላንድ

ኩዊንስላንድ ዛሬ አንድም በቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ አልተመዘገበም።
COVID-19 update
Source: Annastacia Palaszczuk
የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ አሁኑኑ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 9 ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።
  • ኖርዘር ቴሪቶሪ ለአራት ሳምንታት የሚቆይ የ14 ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ ነገ ይጀምራል።
  • የኮቪድ-19 መከላክያ ግብረ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጆን ፍሪዌን የአውስትራሊያ ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ይሁንታን እንዳገኘ ከሙሉ ክትባት ስድስት ወራት በኋላ የማጠናከሪያ ክትባት ዝግጁ እንደሚሆን ገለጡ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 

 



Share
Published 25 October 2021 4:45pm
Updated 25 October 2021 4:54pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends