የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 6.8 ሚሊየን ክቶባቶችን አለፈች

*** "ምንጫቸው ለጊዜው ካልታወቁት በተለይም ሆብሰንስ ቤይ፣ ዊንድሃምና ሂዩም የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች በስተቀር 'አብዛኛው የወረርሽኙ ተዛማችነት በቁጥጥር ስር ነው ያለው'" - የቪክቶሪያ ዋና የጤና መኮንን ፕ/ር ብሬት ሳተን

COVID-19 update

Premier Gladys Berejiklian and NSW Chief Health Officer Dr Kerry Chant during a COVID-19 update in Sydney, Monday, August 30, 2021. Source: AAP

  • ኮቪድ-19 በኒው ሳውዝ ዌይልስ ምዕራብ ትራንጊ ዌስት እና ባይሮን ቤይ ተከሰተ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በአብዛኛው በቫይረስ ተጠቅተው ያሉት ዕድሜያቸው ከ 40 በታች ያሉ ናቸው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ለፋይዘር ክትባት መመዘኛዎችን አሰፋች
  • የከባድ ጭነት መኪና ሾፌሮች ኩዊንስላንድ ውስት ተቃውሞ አሰሙ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,290 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 883ቱ ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

እንደራሴ በርጂክሊያን ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ጎልማሶች ውስጥ ሁለት ሶስተኞቹ የመጀመሪያ ዙር ክትባት መከተባቸውንና 36 ፐርሰንቱ የሁለተኛ ዙር ክትባቶችን መከተባቸውን ተናግረዋል። በወርሃ ኦክቶበር 70 ፐርሰንት ያህል ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ሊከተቡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል።

የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች፣ ዕድሜያቸው ከ16- 39 ሆኖ ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ለሆኑና ነዋሪነታቸው ወይም የሥራ ገበታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሆኖ በሕፃናት ክብካቤ፣ የግብረ አካል ጉዳተኞችና የምግብ ሠራተኞች ዘርፍ ለሆኑ የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ,   and   

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 73 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 21ዱ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም። በጠቅላላው ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረስ ተይዘው ካሉት ሰዎች ውስጥ ሶስት አራተኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ40 በታች ያሉ ናቸው።

ዋና የጤና መኮንን ፕ/ር ብሬት ሳተን ምንጫቸው ለጊዜው ካልታወቁት በተለይም ሆብሰንስ ቤይ፣ ዊንድሃምና ሂዩም የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች በስተቀር 'አብዛኛው የወረርሽኙ ተዛማችነት በቁጥጥር ስር ነው ያለው' ሲሉ ገለጡ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 12 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 

ዋና ሚኒስትር አንድሩ ባር  ዕድሜያቸው ከ16-29 ያሉ "በመጪዎቹ ቀናት" ውስጥ የፋይዘር ክትባትን በመንግሥት የመከተቢያ ክሊኒኮች ውስጥ መከተብ እንደሚችሉ አስታውቁ።

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ መሆንዎን ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የኩዊንስላንድ ከባድ የጭነት መኪና ሾፌሮች በጎልድ ኮስት እና ብሪስበን መካክል የሚገኘውን አውራ ጎዳና ዘግተው ገደቦች እንዲነሱና ወሰኖች እንዲከፈቱ ጠይቀዋል
  • ሁሉም ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 39 ያለ አውስትራሊያውያን የፋይዘር ከትባትን ለመከተብ መመዘኛዎችን እንደሚያሟሉ ተገለጠ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 


Share
Published 30 August 2021 3:35pm
Source: SBS

Share this with family and friends