የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከሰኞ ጀምሮ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎቿ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች

***የቪክቶሪያ ባቡር ግልጋሎት ተገታ

COVID-19 update

Source: AAP

  • ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በቅርቡ ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ባይታወቅም ኮቪድ-19 ተከስቷል
  • የቪክቶሪያ  V/Line ባቡር ግልጋሎት ተገታ
  • አውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ ተጨማሪ የክትባት ቀጠሮ ስንዱ ሆኖ አለ
  • ኩዊንስላንድ አንድ ሰው በቫይረስ የተጠቃባት መሆኑን አስታወቀች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,542 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ በ12ቱ የስጋት አካባቢ መንግሥት ነዋሪዎችን ስያካትት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ  በ12ቱ የስጋት አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑና ሙሉ ክትባት የተከተቡ አብረዋቸው በአንድ ቤት ከሚኖሩ የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር በመሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ለሽርሽር ወይም ለመዝናናት እንዲሁም ላልተወሰነ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከቤታቸው መውጣት ይችላሉ። 

ኮቪድ-19 በታምዎርዝ፣ ላይትኒንግ ሪጅ፣ ግሌን ኢነስ፣ ካልቡራ ቢች እና ሞሩያ የቆሻሻ ፍሰት አካባቢዎች ተከስቶ ተገኝቷል።  

ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊው የ11:00 am ፕሬስ ኮንፈረንስ ምትክ የኦንላይን ቪዲዮ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 334 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 149ኙ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። 

ከሳውዘርን ክሮስ ባቡር ጣቢያ ተነስቶ ወደ ጊፕስላንድ ይጓዝ የነበረ ባቡር ሾፌር በኮሮናቫይረስ በመያዙ ሳቢያ ሃያ የ  ተገትተዋል። የግልጋሎቶቹ መገታት ምናልባትም እስከ 100 ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 24 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል፤ ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

ባለስልጣናት ሰዎች ይቅስያዙትን ቀነ ቀጠሮ ለመለወጥ  እንዲጠቅሙ አሳሰቡ። ከ30,000 በላይ ተጨማሪ ቀጠሮዎች ለተከታቢዎች ክፍት ናቸው።                                                                                                   

ለክትባትዎን ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ብሪስበን ሰኒባንክ በሚገኘው ቅዱስ ቶማስ ሞር ኮሌጅ የታደመ አንድ ታዳጊ ወጣት በቫይረስ መያዙን አስመዘገበች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 


Share
Published 10 September 2021 2:32pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends