- ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች በከፊል ተነሱ
- ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ እንዳይጓዙ ፖሊስ በተጠንቀቅ ይገኛል
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የ CBR ኧፕ ለውጥ አደረገ
- ኩዊንስላንድ አንድ ሰው በቫይረስ ተይዞባታል
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,405 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ሁለት ዙር የኮቪድ-19 ክትባት ለተከተቡ ከፊል የቀድሞ ነፃነቶችን መጠቀም እንደሚችሉ አስታወቁ
በዚህም መሠረት፤ ቤት ውስጥ ታግዶ መቆየት አይኖርም፣ ሁሉም አዋቂዎች ሙሉ ክትባት የተከተቡበት ቤት ውስጥ እስከ አምስት የሚደርሱ እንግዶችን ማስተናገድ ይቻላል። የመስተንግዶ ሥፍራዎች፣ የችርቻሮ ሱቆች፣ የስፖርት ሥፍራዎች፣ እንዲሁም ለአንድ ሰው በ 4 ስኩየር ሜትር ርቀት መስፈርት የፀጉር ቤቶችና የጥፍር ሳሎኖችን የመሳሰሉ የግል ግልጋሎት መስጭያዎች ክፍት ይሆናሉ።
ከሴፕቴምበር 11 ጀምሮ ላለፉት 14 ቀናት ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነው የቆዩ የሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ አካላት ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ይረግባሉ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 324 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 107ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው።
ሴፕቴምበር 9 እኩለ ለሊት ላይ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ ሲረግብ የሜልበርን ነዋሪዎች ወደዚያ እንዳያመሩ ለመቆጣጠር የቪክቶሪያ ፖሊስ ስምሪቱን ከፍ አድርጓል።
ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ ሕጋዊ ያልሆነ ጉዞ የሚያደርጉ ተጓዦች እስከ $5,5000 መቀጮ ያገኛቸዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 15 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል፤ ስምንት ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
አዲስ የተሻሻለው ተጠቃሚዎች ተጋላጭ አካባቢዎች መገኘታቸውን የሚያሳውቅ መልዕክት እንዲደርሳቸው ያደርጋል። እንዲሁም ጮሌ ስልክ (martphone) የሌላቸው መጠቀም ይችላሉ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤