- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ዕድሚያቸው ከ12 በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሐኪሞች ዘንድ መከተብ ይችላሉ
- ኮቪድ-19 ቪክቶሪያ ውስጥ በባቡር ግልጋሎቶች ላይ ብርቱ መስተጓጎልን አስከትሏል
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መከተብ እንደሚችሉ አስታወቀች
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ተመዘገበ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,257 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ቫይረስ በይበልጥ የተስፋፋባቸው ክፍለ ከተሞች Greenacre, Auburn, Yagoona, Liverpool, Punchbowl, Guildford, Redfern, Bankstown, Condell Park and Busby መሆናቸው ሲገለጥ፤ በግሌብና ረድፈርን ክፍለ ከተሞች በየዕለቱ በቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሔዱም ተነገሯል።
ከዛሬ ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያለ ልጆች ጠቅላላ ሐኪሞች ዘንድ መከተብ የሚችሉ ሲሆን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮም ሞደርና ክትባትን በየመድኃኒ ቤቶች መከተብ ይቻላል።
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች በቡድን እስከ አምስት ሆነው መገናኘት ይችላሉ።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 473 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።
ትናንት ለሊቱን አራት የሜልበርን ሕፃናት ክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ተጋላጭነት ዘርፍ ተፈርጀዋል። አምስት V/Line ባቡር ሾፌሮች በቫይረስ በመያዛቸው ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ራሳቸውን እንዲያገሉ በመደረጉ ብርቱ የባቡር ግልጋሎቶች መስተጓጎል ተከስቷል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
13 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተየዘዋል።
ከሴፕቴምበር 20 ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 የሆነ ልጆች በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ መንግሥት ክሊኒክ ዘንድ የክትባት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ከአንድ የብሪስበን ትምህርት ቤት ጋር ተያይዞ በቫይረስ ከተጠቃችው ግለሰብ ጋር ንኪኪ ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በቫይረስ ተያዙ
- የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ ሞደርና ክትባትን እንዲከተቡ ምክረ ሃሳቡን ሰጠ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤