- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ነርሶች ክብካቤ የሚሰጧቸው ሕሙማን ቁጥር አግባብ ያለው እንዲሆኑ የተሻለ ክፍያ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ የሥራ ማቆም አድርገው የተቃውሞ ሰልፍ አካሔዱ። የተቃውሞ ሰልፉን ያካሔዱት ዛሬ ማለዳ ከ 7am የጀመረ ሲሆን ለሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ቀጥሎ ይውላል።
- የተቃውሞ ሰልፉ የተካሔደው ሲድኒ ፓርላማ ፊት ለፊት ነው።
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ሚኒስትር የኢንዱስትሪ ግንኙነቶች ኮሚሽን ሰልፉ እንዳይካሔድ ትዕዛዝ የሰጠው ቢሆንም የሠራተኛ ማኅበሩ አሌ ብሎ ሰልፉን ማካሄዱ "ቅር አሰኚ" እንደሆነ ገልጠዋል።
- በሥራ ማቆሙ እርምጃ ወቅት ሕይወት አዳኝ የሆኑ ግልጋሎቶች በሕዝብ ሆስፒታሎችና የጤና አገልግሎቶች መስጠታቸው ሳያቋርጥ ይቀጥላል።
- ኖቫቫክስ ክትባት በጠቅላላ ሐኪም ክሊኒኮች፣ መድኅኒት ቤቶችና በመንግሥት የሚካሔዱ የክትባት ማዕከላት ውስጥ መስጠት ተጀምሯል።
- ክትባቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ የመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባትነት እንዲውል ይሁንታን አግኝቷል። በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑና ለሶስተኛ ዙር ክትባትነት እንዲውል ይሁንታን አላገኘም።
- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የኖቫቫክስ ክትባት "ለመከትብ እየጠበቁ ላሉ ወይም ሌላ ክትባቶችን ለመከተብ ላልቻሉ" "አዲስ አማራጭ" እንደሚሆን ገልጠዋል።
- የ ድረገጽ በመላ አውስትራሊያ ኖቫቫክስን የት ማግኘት እንደሚቻል መረጃን ይሰጣል።
- የቪክቶሪያ ተቃዋሚ ቡድን መሪ ማቲው ጋይ የቪክቶሪያ ፓርላማ ውስጥ የፊት ጭምብል ባለማጥለቃቸው የ $100 መቀጮ ተጣለባቸው። ሌሎች አራት የምክር ቤት አባላትም እንዲሁ ተመሳሳይ መቀጮ አግኝቷቸዋል።
- ቪክቶሪያ አዲሱ ዓመት ከገባ ወዲህ ዝቅተኛ የኮቪድ-19 የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር አስመዘገበች።
- የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል በኮቪድ 19 ለተጠቁ ሶስት የታዝማኒያ አረጋውያን ተቋማት እገዛ እንደሚያደርጉ ምክትል ፕሪሚየርና የጤና ሚኒስትር ጀርሚ ሮክሊፍ አስታወቁ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 8,201 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ16 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,583 ሕመማን 96 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 8,162 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 20 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 441 ሕመማን 67 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 14 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 3,750 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 10 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 462 ሕመማን 35 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 16 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
ታዝማኒያ 513 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 10 ሕሙማን መካክል አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።
ደቡብ አውስትራሊያ 1,138 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 219 ሕመማን 18 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 5 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ