- ቪክቶሪያ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ ጥላ የነበረውን የወሰን ገደብ አነሳች
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ አስቸኳይ ያልሆኑ ቀዶ ሕክምና ግልጋሎት ሊቀጥል ነው
- 24 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቁ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,841 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ቪክቶሪያ ውስጥ እስካሁን በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 22,598. ደርሷል።
ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ክትባት የተከተቡ የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንገደኞች ቪክቶሪያ ሲገቡ ወሸባ እንዲገቡ ግድ አይሰኙም።
ይሁንና Blue Mountains, Central Coast, Shellharbour እና Wollongong መንገደኞች ወደ ቪክቶሪያ ለመዝለቅ የብርቱካንማ ዞን ይለፍ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል።
ሙሉ ክትባት ያልተከተቡ ሰዎች ቪክቶሪያ እንደገቡ ራሳቸውን ማግለልና በ72 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ በማካሄድ ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚያመላክት ማስረጃ እስኪያገኙ ድረስ ተገልለው መቆየት ይጠበቅባቸዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 283 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መስፋፍትን ተከትሎ ሲድኒ ላይ ለሁለት ወራት ተገትቶ የነበረው አስቸኳይ ያልሆነ ቀዶ ሕክምና በሚቀጥለው ሳንት ይጀምራል።
ከሰኞ ጀምሮ ብሉ ማውንቴንን አካትቶ ሲድኒ ውስጥ ያሉ የሕዝብና የግል ጤና ተቋማት ከአቅማቸው 75 ፐርሰንት ያላለፈ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ይችላሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ካንብራ ውስጥ ባሉ የቤት ውስጥ ውስጥና የማኅበረሰብ አረጋውያን መጠወሪያዎች ውስጥ የሚሠሩና የግብረ አካል ጉዳተኞች ድጋፍ ሠራተኞች ላይ ክትባት የመከተብ ግዴታን ጣለች።.
- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ዕድሚያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ያሉ ሙሉ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 70 መድረሱን አስታወቁ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤