- ከዛሬ ሰኞ 5pm አንስቶ ሙሉ ክትባት የተከተቡ፣ ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ነፃ የመሆናቸው ማረጋገጫ ያላቸው ለ14 ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ መግባት የሚፈቅዱ ሰዎች ወደ ኩዊንስላንድ በአየር መጓዝ ይችላሉ። ኩዊንስላንድበሯን ለጎብኚዎች የከፈተችው ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት በመድረሱ ነው።
- ደቡብ አውስትራሊያ በሚቀጥለው ሳምንት እንደታሰበው ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎቿ ቁጥር 80 ፐርሰንት ከደረሰ በኋላ ገደቦችን እንደማትጥል አስታወቀች።
- የቪክቶሪያ መንግሥት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እንዲያግዝ ፈጣን የመመርመሪያ ቁሶችን ለሙዋዕለ ሕፃናትና የረጅም ቀን የሕፃናት ክብካቤ ለሚሰጡ ማዕከላት በዚህ ሳምንት አከፋፈለ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 860 በቫይረስ ሲጠቁ፤ አምስት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 165 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤