- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ለ80 ፐርሰንት የክትባት መጠን ተለሙ
- ኩዊንስላንድ ውስጥ በዴልታ ቫይረስ የተቁ ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 18 ደረሰ
- ቪክቶሪያ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
- ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ አውስትራሊያውያን ውስጥ አርባ ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 239 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባትና 61 ያህሉ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት እንደሆነ ገለጠች። ከተያዙት ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የቫይረሱ ምንጭ ገና አልተለየም።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ተወካይ ዶ/ር ጀርሚ ማክአነልቲ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው የፅኑዕ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ ሕክምና እየተደረገላቸው ካሉት 54 ሰዎች ውስጥ 49ኙ ክትባት ያልተከተቡ እንደሆኑ ተናገሩ።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት የብሔራዊ ካቢኔው ከአዋቂ አውስትራሊያውያን ውስጥ ከ70 እስከ 80 ፐርሰንት የመከተብ ትልምን መቀበሉን ገለጡ።
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት ዘጠኝ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን አስመዝግባለች። ቁጥሩ ከአንድ ዓመት በላይ ኩዊንስላንድ ውስጥ ከተከሰተው የላቀ ነው።
የኩዊንስላንድ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ “ቁጥሮቹ በፍጥነት እያሻቀቡ ነው” ብለዋል። አክለውም፤ የማኅበረሰብ አባላት ምርመራ እንዲያካሂዱ አበረታተዋል።
ቫይረሱ የተስፋፋባቸው የደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ አካባቢዎች ለሶስት ቀናት ገደብ ተጥሎባቸው ያሉ ሲሆን የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ ሁኔታዎች ያሟሉ ሆነዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ቪክቶሪያ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
- ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ አውስትራሊያውያን ውስጥ አርባ ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት መከተባቸውን አንድ አዲስ አሃዛዊ ሪፖርት አመለከተ
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤