የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኩዊንስላንድ የ80 ፐርሰንት ኮቪድ- 19 ገደቦች ማርገቢያ ፍኖተ ካርታዋን ይፋ አደረገች

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 1,069 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 10 ሕይወታቸውን አጥተዋል።

COVID-19 update

Kiongozi wa Queensland Annastacia Palaszczuk (katikati), akizungumza na wafanyakazi katika kituo cha chanjo cha Logan. Source: AAP

  • ኩዊንስላንድ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎች የተለያዩ ገደብ ማርገቢያዎችን ይፋ አደረገች።
  • ከዲሴምበር 17 ወይም ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ በመጠጥ ቤቶች፣ ሌሎች መዝናኛዎች፣ ስታዲየሞችና መሰል ሥፍራዎች ላይ ገደቦች አይኖሩም።
  • የሆስፒታል ጉብኝቶች የሚፈቀዱት ሙሉ ክትባቶችን ለተከተቡ ብቻ ይሆናል፤ ላልተከቡ ሰዎች ልዩ የሆስፒታል ጉብኝት ፈቃድ የሚሰጠው ሊጎበኙት የሚሹት ሰው የሕይወት ፍፃሜ ላይ ወይም ድንገተኝ አደጋ ላይ ያለ ከሆነ ብቻ ይሆናል።
  • ሙሉ ክትባት የተከተቡ የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች የፊት ጭምብል ለማጥለቅ ግድ የሚሰኙት በበረራ ወቅትና አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ይሆናል። 
  • ባለ ሶስት ደረጃ ፍኖተ ካርታን ተመርኩዞ ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ ከኖቬምበር 23 ጀምሮ የቤት ውስጥ ወሸባ ይጀመራል።

የኮቪድ-19 ተጠቂዎች፤

  • ቪክቶሪያ ውስጥ 1,069 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 10 ሕይወታቸውን አጥተዋል።
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ 222 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውንና አራት ለሞት መዳረጋቸውን አስመዘገበች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 

 


Share
Published 9 November 2021 6:59pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends