የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ኮሮናቫይረስ እያሻቀበ ገደቦች እየጠበቁ ነው

*** ቪክቶሪያ ውስጥ ስድስት ደቡብ አውስትራሊያ ሁለት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል

A near empty Market Street is seen in the central business district in Sydney, Thursday, July 29, 2021.

A near empty Market Street is seen in the central business district in Sydney, Thursday, July 29, 2021. Source: Getty


  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የቅርቡ ወረርሽኙ መስፋፋት ከጀመረ ወዲህ ከፍተኛ ሬኮርድ ያለው ቁጥር አስመዝግባለች
  • ቪክቶሪያ እስካሁን ግኝቱ ያልተፈረጀ አንድ የቫይረስ ጥቃት ላይ ምርመራ እያካሔደች ነው
  • ደቡብ አውስትራሊያ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተውባታል
  • የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች ላይ የአንድ ሳምንት የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታ ተጣለ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 239 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተጠቁባትና ሁለት ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉባት መሆኑን አስታወቀች። ሟቿ አረጋዊት ዕድሜያቸው በ90ዎቹ ያለ ሲሆን ሟቹ አረጋዊ ዕድሜያቸው 80ዎቹ ውስጥ የነበረ ነው። ሁለቱም የደቡብ ምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎች ነበሩ። የ126 ተጠቂዎች እንደምን ቫይረሱ እንዳገኛቸው እየተጠና ሲሆን 81ዱ ብቻ ወሸባ ውስጥ ነበሩ። 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን በስምንት ቫይረሱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች ፌይርፊልድ፣ ካንተርበሪ፣ ባንክስታውን፣ ሊቨርፑል፣ ካምበርላንድ፣ ብላክታውን፣ ፓራማታ፣ ካምፕቤልታውንና ጆርጅ ሪቨር ያሉ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ከአምስት ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቀው መሔድ እንደማይችሉ አስታውቀዋል።

ኒው ሳዝ ዌይልስ ውስጥ የፊት ጭምብል ያለማድረግ መቀጮ ክ$200 ወደ $500 ከፍ ተደርጓል። ከነገ ጀምሮ በተደጋጋሚ ሕግ የሚጥሱ ንግድ ቤቶችን የመዝጋት ስልጣን ለፖሊስ ተሰጥቷል። 

ለውጥ የተደረገባቸውን መመሪያዎች እዚህ ይመልከቱ 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ ስድስት ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸውን በዛሬው ዕለት ተመለከተ። ሁሉም በዴልታ ቫይረስ የተጠቁና ወሸባ ያሉ መሆናቸው ተገልጧል። 

የጤና ባለስልጣናት አሁንም ድረስ ትናንት የተከሰተውን የአንድ ቫይረስ ምንጭ ለማጣራት ምርመራ እያካሔዱ ነው።

የተሻሻሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እዚህ ይመልከቱ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ደቡብ አውስትራሊያ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ሲሆን፤ ሁለቱም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።
  • በ  ነዋሪዎች ለተጨማሪ አንድ ሳምንት የፊት ጭምብል አጥልቀው መቀጠል ግድ ይላቸዋል።

ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share
Published 29 July 2021 5:54pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends