የኒው ሳውዝ ዌይልስ 825 ነዋሪዎች በኮቪድ-19 ተጠቁ

*** ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ከዛሬ ከቀትር ሰዓት በኋላ ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጣለ

COVID-19 update

Source: AAP

  • ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 61 ሰዎች በቫይረስ ተይዘውባታል፤ በመላው ክፍለ አገሪቱ ላይ ገደብ ተጥሏል 
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ተመዘገበ 
  • ኩዊንስላንድ አንድም ሰው በቫይረስ ያልተያዘበትን ሁለተኛ ቀን አስቆጠረች 
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት ሲሆን አንዳቸውም የማኅበረሰብ ተጋቦት አይደሉም 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች፤ የሶስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሟቾቹ አንድ 90ዎቹ ውስጥ የነበሩና ያልተከተቡ አረጋዊ፣ አንድ በ80ዎቹ የነበሩ ሙሉ ክትባት የተከተቡና አንዲት በ90ዎቹ ዕድሜ ያሉና አንድ ጊዜ ብቻ የተከተቡ አረጋዊት ይናቸው። 

  ቫይረስ ተስፋፍቶ ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ሥፍራዎች ነዋሪ ሆነው ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 39 ያሉ ግለሰቦች የኮቪድ-19 ፋይዘር ቀጠሮ አስይዘው መከተብ ይችላሉ። 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 61ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 39ኙ ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።

ሪጂናል ቪክቶሪያ ውስጥ በርካታ ሰዎች በቫይረስ መያዝን ተከትሎ ከዛሬ 1pm ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ገደብ ተጥሏል። 

ከሰዓት ዕላፊ በስተቀር ሜልበር ላይ ተጥለው ያሉት ገደቦች በሙሉ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ የፀኑ ይሆናሉ።  

የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ  በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ


Share
Published 21 August 2021 2:36pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends