የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ ከኮሮናቫይረስ ገደቦች የመውጫ ፍኖተ ካርታዋን ይፋ አደረገች

*** ኩዊንስላንድ በአንድ ቀን ውስጥ አዲስ የክትባት ሬኮርድ አስመዘገበች

COVID-19 update

People are seen having a picnic at Albert Park Lake in Melbourne, Sunday, September 19, 2021. Source: AAP

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ አሳሳቢ የአካባቢ መንግሥት ክፍለ ከተሞች ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች መርገባቸውን አስታወቁ
  • ቪክቶሪያ ከገደቦች የመውጫ ፍኖተ ካርታዋን ይፋ አደረገች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 17 ነዋሪዎች በኮቪድ-19 ተጠቁ
  • ኩዊንስላንድ በአንድ ቀን ውስጥ አዲስ የክትባት ሬኮርድ አስመዘገበች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,083 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 13 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ከሰኞ ሴፕቴምበር 20 ጀምሮ ሁሉም የአሳሳቢ አካባቢ መንግሥት ክፍለ ከተሞች ከተቀረው የሲድኒ ክፍለ ከተሞች ጋር በተመሳሳይ ድንጋጌ ስር እንደሚሆኑ አስታወቁ። ፈቃድ ያላቸው ሠራተኞችና የጉዞ ፈቃድ መመሥፈርቶች ፀንተው የሚቆዩ እንደሆነም አሳስበዋል 

በመላው ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከቤት ውጭ ያሉ የመዋኛ ሥፍራዎች የኮቪድ-ጥንቃቄ ፕላን ይሁንታ ያላቸው በመሆኑ ከሰኞ ሴፕቴምበር 27 አንስቶ ግልጋሎት መስጠት ይጀምራሉ። 

በአሁኑ ወቅት የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉ የኒው ሳውዝ ነዋሪዎች ውስጥ 81.9 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 51.9 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ተከትበዋል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 507 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ባለ አምስት ደረጃ ከገደቦች መውጫ ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረጉ። እንደታሰበው ኦክቶበር 26 የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉት ውስጥ 70 ፐርሰንት የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ከተከትቡ ተጥለው ያሉ ገደቦች እንዲያከትሙ ይደረጋል።

አቶ አንድሩስ ዕቅዱን አስመልክተው "ዳግም ክፍት እንሆናለን፤ ወደ ኋላ መመለስ አይኖርም" ብለዋል። የ80 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት የተያዘለትን ዕቅድ ከመታ በገና ዕለት እስከ 30 እንግዶችን በቤት ውስጥ ማስተናገድ ይቻላል።   

ዳታዎች እንደሚያመለከቱት ከሆነ 71.2 ፐርሰንት ያህል የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር  የኮቪድ-19 ክትባቶችን፤  43.5 ፐርሰንት ሙሉ ክትባቶችን ተከትበዋል። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

Share
Published 19 September 2021 2:51pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends